መነሻ ገጽ መከላከያ የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ ነገም ቀጥሎ ይካሄዳል !!
መከላከያአዲስአበባ ከተማኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየአዲስአበባ ከተማ ዋንጫጅማ አባጅፋር

የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ ነገም ቀጥሎ ይካሄዳል !!

አጋራ
አጋራ

ከመስከረም 15 ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተከናወነ የሚገኘዉ የአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ መካሄዳቸዉን ይቀጥላሉ።

በምድብ አንድ የተደለደሉት አዲስአበባ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር 8:00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸዉን የሚያደርጉ ሲሆን ምድብ አንድን ከመከላከያ ጋር በእኩል ሶስት ነጥብ በመምራት ላይ የሚገኙት ተጋባዦቹ ጅማዎች የመጀመሪያ ጨዋታቸዉን ኢትዮጵያ ቡናን በዳዊት ፍቃዱ እና መሀመድ ኑር ግቦች ታግዘዉ ሁለት ለዜሮ ካሸነፉ በኋላ በነገዉ ዕለት ሌላኛዉን የመዲናዉን ክለብ አዲስአበባ ከተማ የሚገጥሙ ይሆናል።

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታም ቀን 10:00 ላይ የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ በጅማ አባጅፋር የተሸነፉት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከ ሌላኛው የከተማዉ ክለብ መከላከያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል። በመክፈቻ ጨዋታው በርከት ያሉ ወጣት ተጫዋቾችን የተጠቀሙት ቡናማዎቹ በነገዉ ዕለት የመጀመሪያ ሶስት ነጥባቸዉን ለማሳካት ከመከላከያ ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው የሚጠበቅ ሲሆን በአንፃሩ በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመሩት መከላከያዎች ደግሞ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸዉንም በድል ለመወጣት ወሳኙን ግጥሚያ ከቡናማዎቹ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...