የአዳማ ከተማ ቀጣይ አሰልጣኝ ማንነት ውዝግብ ፈጥሯል
…የቀድሞ አሰልጣኝ አስቻለሁ ሀ/ሚካኤል
ከክለቡ ተሰናብተዋል
አዳማ ከተማ ውጤታማ እለመሆኑን ተከትሎ በአሰልጣኝ አስቻለሁ ሀ/ሚካኤል ምትክ ማን ሊሾም ይገባል የሚለው ውዝግብ ያስነሳ ሲሆን አሰላጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው፣አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃምና አሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ማን ቦታውን ይረከብ የሚለው አዲሱን የክለቡ ፕሬዝዳንትና የክለቡ ማህበረሰብ መሃል አለመግባባት እንዳይፈጥር ተሰግቷል።
ገና ሃላፊነቱን ከያዙ ሳምንት ያልሞላቸው ፕሬዝዳንቱ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ አዲሴ ካሳን ለመሾም ሲያስቡ የቴክኒክ ኮሚቴውና ሌሎቹ አመራሮች ግን አሰልጣኝ ጳውሎስና አሰልጣኝ ሲሳይ መሃል አንዳቸው እንዲሆኑ አወዳድረው ለውሳኔ ማቅረባቸውን ተከትሎ አለመግባባት እንዳይከሰት ተሰግቷል። ፕሬዝዳንቱ በባለሙያዎች የቀረበላቸውን ከማየት በግላቸው መወሰናቸው ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባት ነው የሚሉ የክለቡ ሰዎች ቅሬታ እያሰሙ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ክለቡን ውጤታማ ማድረግ እልቻሉም በሚል አሰልጣኝ አስቻለሁ ሀ/ሚካኤል መሰናበታቸው ተሰምቷል። አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ማሸነፍ ካልቻሉ እንደሚሰናበቱ በደብዳቤ ተገልጾላቸዋል በጊዮርጊስ 4 ለ 2 ከተረቱ በኋላ ሁለተኛ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው ቡድኑን ባህርዳር ትተው ወደ አዳማ ሊመለሱ ሲሉ በኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ሰዎች በሰጡት ማሳሰቢያ ቀርተው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የተደረገውን ጨዋታ መምራታቸው ከክለቡ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የተገኘ መረጃ ያስረዳል።
የአዳማ ከተማ አሰልጣኝነትን ለመረከብ ከቀድሞ የሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ጋር የተነጋገሩ ቢሆንም ሳይሳካ መቅረቱን ያገኘነው ማስረጃ ያስረዳል።
አስተያየት ይስጡ