መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ “በሁለተኛው ዙሩ ከአንደኛው ዙር የተሻለውን ጅማ አባጅፋር እንደምታዩት ተስፋ አለኝ” ተመስገን ደረሰ /ጅማ አባጅፋር /
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችጅማ አባጅፋር

“በሁለተኛው ዙሩ ከአንደኛው ዙር የተሻለውን ጅማ አባጅፋር እንደምታዩት ተስፋ አለኝ” ተመስገን ደረሰ /ጅማ አባጅፋር /

አጋራ
አጋራ

“ከወራጅ ቀጠናው የምንወጣበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ”

“በሁለተኛው ዙሩ ከአንደኛው ዙር የተሻለውን ጅማ አባጅፋር እንደምታዩት ተስፋ አለኝ” ተመስገን ደረሰ /ጅማ አባጅፋር /

 

የእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑን የጀመረው በጅማ አባ ቡና ቤት ነው ለወልቂጤ ከተማ ተጫውቶ አሳልፏል። ከአምና ጅምሮ ለጅማ አባጅፋር ፊርማውን አኑሮ በመጫወት ላይ ይገኛል።

ይሄ ሁለገብ የሆነው ተጨዋች ተመስገን ደረሰ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በጅማ ዞን አሰንዳቦ ከተማ ነው። በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ለጅማ አባጅፋር ሶስት ግቦችን በማስቆጠር የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪው ተጨዋች ጋር ሀትሪክ ስፖርት ድረ-ገፅ ያደረገችው ቆይታ ይህንን ይመስላል።

ሀትሪክ:- የሲዳማ ቡና ጨዋታ እንዴት ነበር?

ተመስገን:- ከሱ ጨዋታ በፊት ቡድኑ ውስጥ ያለው አብዛኛው ነገር ተስተካክሎ ስለ ነበር ጨዋታውን በጥሩ መንፈስ ነው የጀመርነው እና ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረገውን ጨዋታ በጣም ከባድ ነበር ምክንያቱም እኛም እነሱም በአዲስ አስልጣኝ ነው ወደ ሜዳ የገባው እና ፈጣሪ ብሎ እኛ የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ ይዘን ከሜዳ መውጣት ችለናል።

ሀትሪክ:- ጅማ አባጅፋር የገጠመው የውጤት ማጣት ጊዜያዊ ነው? ወይንስ ዘለቄታዊ….

ተመስገን:- አሁን ማሸነፍ ጀምረናል እና እሱን ለማስቀጠል ነው ምንጫወተው። ጊዛው ነው ምክንያቱም በጥቃቅን ስተቶች ነው ዉጤት እያጣን የመጣነው በርግጠኝነት በ2ኛው ዙር ነገሮችን ተስተካክለው ውድ አሸናፊነት እንመለሳለን።

ሀትሪክ:- ሀዲያ ሆሳዕና ከጅማ አባጅፋር ጋር ስለምታደርጉት ቀጣይ የሊግ ጨዋታ?

ተመስገን:- ጥሩ የሆነ መነሳሳት አለ ቡድኑ ውስጥ እና በጥሩ መንፈስ ጨዋታውን እንደምናደርገው ከዝህ በፊት ካደረግናቸው ጨዋታዎች በተለይ ነው የምንጫወተው።

ሀትሪክ፡- በቤት ኪንጉ ዘንድሮ ስኬትን እያስመዘገበ ካለው ሀዲያ ሆሳዕና ጋር የምታደርጉት ቀጣይ ጨዋታ ይጠበቃል? ማን ጨዋታውን በድል ይወጣል?

ተመስገን:- አዎ ሀዲያ ሆሳዕና ጥሩ ጅማሬ አድርጎአል እኛ ደሞ አሁን ላይ ጥሩ መነሳሳት ላይ ነን እና ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ለሚለው ከ90ደቂቃ በኃላ ነው ሚታወቀው ግን እኛ ለማሸነፍ የሚቻለውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን

ሀትሪክ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ምን የተለየ ነገርን ተመለከትክ?

ተመስገን:- ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የተመለከትኩት ጨዋታዎች በዲኤስ-ቲቪ መተላለፋቸው ለተጨዋቾች አሪፍ እድል ነው አሪፍ ፐርፎም ያደረገ ተጫዋች በሌላ ቡድን የመታየት እድል በቀላሉ ይገኛል ብዬ አስባለሁ።

ሀትሪክ:-በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመክ ያዘነክበት ጊዜ?

ተመስገን:- ከአንድም ሁለት ነው በእግር ኳስ ህይወቴ ያዘንኩት አንደኛው 2007 ድሬዳዋ ከተማ አባ ቡናን አሸንፎ ወድ ፕሪሚየር ሊግ ሲያድግ እኛ አራት ውስጥ ገብተን እና ጅማ አባ ቡና ፕሪሜርሊግ በገባበት አመት 2009 በዛው አመት ከፕሪሚየር ሊጉ የወረድንበት ጊዜዎች ናቸወ።

ሀትሪክ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ያለፉት ጊዜ
ጨዋታዎቻችሁ በጣም የተቆጫችሁበት ነገር አለ?

ተመስገን:- አዎ በጣም የተቆጨውባት ጨዋታ አለ በተለይ የሀዋሳ ጨዋታ እና የሰበታው ጨዋታ ከ80ደቂቃ በላ ጎል ተቆጥረውብን አቻ የወጣነው ጨዋታ

ሀትሪክ፡- ቤት ኪንጉ ላይ የቱ ተጨዋች ጎልቶ ወጣብህ?

ተመስገን:- የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር ጎል እያገባም አጨዋወቱም በጣም ደስ ይላልና እሱን ነው ዘንድሮ ጎልቶ የወጣ ተጨዋች የምለው”።

ሀትሪክ፡- ተመስገን ዘንድሮ ይለያል?

ተመስገን፡- ስለራሴ እንዲህ ማለትን አልፈልግም፤እሱን ለተመልካች ትቻለሁ ፈገግ እያለ፡፡

ሀትሪክ:- ስለ ደጋፊዎች?

ተመስገን:- ሰለ ደጋፊው ከምንናገረው በላይ ድርጊታቸው የሚታይ ነገር ነው ሰለ እነሱ ቃላት ያጥረኛል ወጤት መጣም አልመጣም ሁሌም ከጎናችን ናቸው። ቡድኑን ከልባቸው ነው ሚወዱት ጅማ አባጅፋር ቡድኑ በሄደበት ቦታ ሁሉ እየሄዱ ሲያበረታቱን ነበር ምስጋና ይገባቸዋል።

ሀትሪክ :- በመጨረሻም…

ተመስገን :- በእግር ኳሱ ትልቅ ደረጃ የመድረስ እልም አለኝ።
ለዛም ገና ወጣት ስለሆንኩ ጠንክሬም እየሰራው ነው። ይህን ካልኩ ለእስካሁኑ ለደረስኩበት ደረጃ በብዙ ነገር ለረዱኝ ፈጣሪዬ፣ ቤተሰቦቼ፣ ጓድኞቼን ከልብ አመሰግናለሁ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...