ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ስምምነት ፈፅሞ የነበረው አሰልጣኝ የቀድሞው ክለቡን ተቀላቀለ።
የሀድያ ሆሳዕና ቦርድ ከቀናት በፊት ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ባደረገው ስብሰባ ለሁለት አመት ክለቡን ለማሰልጠን መስማማቱ የሚታወቅ ቢሆንም አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ወይም ደጉ ዱባሞን ለመቅጠር በሂደት ላይ የነበረውን አዳማ ከተማ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ሾሟል።

ከተጫዋችነት እስከ አሰልጣኝነት ቅዱስ ጊዮርጊስን ያገለገሉት እና ዘንድሮ ክለቡን ከበርካታ ፈተናዎች ጋር በመታገል ለስኬት አብቅተው ያጠናቀቁት የቀድሞው የባህርዳር ከተማ ፣ መቻል እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ያገለገለው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከአራት አመት በኋላ በመመለስ አዳማ ከተማን በድጋሚ ለማሰልጠን በሁለት አመት ውል መቀላቀል ችሏል።
አስተያየት ይስጡ