የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ዲሲፕሊን ኮሚቴ በምንተስኖት አዳነ ክስ አዳማ ከተማ ላይ የሰጠውን ውሳኔ አጸና።
ዲሲፕሊን ኮሚቴ የካቲት 9/2014 ላይ ባወጣው የውሳኔ ደብዳቤ ክለቡ የዲሲፕሊን ኮሚቴን ውሳኔ በመቃወም ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታን መመልከቱን ገልጾ ነገር ግን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በሰጠው ብይን ላይ የህግ ስህተት፣ ከስልጣን በላይ የተሰጠ ብይን እንዲሁም የፍሬ ነገር ስህተት አላየሁም ብሏል።
በዚህም በዲሲፕሊን መመርያ አንቀጽ 90 ተራ ቁጥር 2 መሠረት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ስህተት አለበት ብሎ ስለማያምን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በክለቡ ላይ የሰጠው ብይን መጽናቱን አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ተጨዋቹ ወደ ስራው እንዲመለስና ቀሪ ደመወዙ እንዲከፈለው የተሰጠው ውሳኔ ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ