በአቤኔዘር አበበ
ሀላባ ከተማና ፋሲል ከነማ ነጥብ ተጋሩ!

በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ሀላባ ከተማና ፋሲል ከነማ 1ለ1 በሆነ ውጤት ተለያዩ።በተመጣጣኝ ፉክክር በታጀበው የመጀመሪያ አጋማሽ ሀላባ ከተማ በ12ኛው ደቂቃ ፍሬው ሰለሞን ከማዕዘን ያሻማውን ኳስ ካሌብ አማንክዋህ በግንባሩ ገጭቶ በመምታት መሪነቱን ያዘ።ከዕረፍት መልስ ግን ፋሲል ከነማ በ49ኛው ደቂቃ የሀላባ ከተማን የተከላካይ መስመር መዘናጋት ተጠቅሞ ሮማሪክ ዲንሆ ባስቆጠረው ግብ ወደ ጨዋታው ተመልሰዎል ።ከዚያ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ቢጥሩም፣ የግብ ጠባቂዎቹ ተጨማሪ ግቦችን በማዳን ጨዋታው 1ለ1 እንዲጠናቀቅ አደረጉ።
ሀላባ ከተማ 1–1 ፋሲል ከነማ
⚽️ 12′ ካሌብ አማንክዋህ
⚽️ 49′ ሮማሪክ ዲንሆ
አስተያየት ይስጡ