መነሻ ገጽ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የክለቦች ዝግጅት | ፋሲል ከነማ
ቅድመ ውድድር ዝግጅትዜናዎችፋሲል ከነማ

የክለቦች ዝግጅት | ፋሲል ከነማ

አጋራ
አጋራ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ፋሲል ከነማ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መሪነት በሊጉ መልካም አጀማመሮችን ያስመለከቱን ፋሲል ከነማዎች በጠንካራ የቡድን ግንባታ የዋንጫ ተስፋ ያለው እስኪመስሉ ድረስ ቢጓዙም በድንገት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሳልፈው ከሰጡ በኋላ ግን ለጥቂት ጨዋታ በረዳት አሰልጣኞች የኋላ ኋላ ደግሞ በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ እየተመሩ በመጠኑ መቀዛቀዞችን እያሳዩን ነገር ግን ከደረጃ ሰንጠረዡ የላይኛው ቦታ ብዙም ሳይርቁ አመቱን አጠናቀዋል። በፕሪምየር ሊጉ ቡድኑ ካደረገው 38 ጨዋታዎች 14 ጨዋታዎችን በማሸነፍ 13 የአቻ ውጤት በማስመዝገብ እና በ11 ደግሞ ሽንፈት በማስተናገድ 28 ጎል በማስቆጠርም ሆነ በተቃራኒው በማስተናገድም ያለምንም የግብ ክፍያ 55 ነጥቦችን በመያዝ የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን 4ተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

ለ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ ሊጉ በማሳደግ በክለቡ የታሪክ ማህደር ውስጥ ሰፍረው የሚገኙት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ውላቸው ከተራዘመላቸው በኋላ በመቀጠል ክረምቱ የጀመረው የአሰልጣኝ ቡድን አባላቱን በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ራሱን ለማሳደግ በስልጠና የበቃውን ኢንስትራክተር መብራቱ ሀብቱን እና ግርማይ ኪሮስን በረዳት አሰልጣኝነት ቦታ በመሾም በዝውውር ገበያውም 8 አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው አካተዋል።

ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾችን ስንመለከት አማካዩ ዮሴፍ ዮሐንስን ከሲዳማ ቡና ፣ አጥቂው አዲስ ግደይን ከንግድ ባንክ ፣ ተከላካዩ ፍሬዘር ካሳን ከመቐለ 70 እንደርታ ፣ አማካዩ ቡታቃ ሸመናን ከአርባምንጭ ከተማ ፣ ግብ ጠባቂው አብዩ ካሳዬን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬ ከምድረገነት ሽረ በኢትዮጵያ መድን ባህርዳር እና የተጠናቀቀውን አመት በአርባምንጭ ከተማ ያሳለፈው ናይጄሪያዊውን አጥቂ ጄሮም ፊሊፕን እንዲሁም የቤኒን ዜግነት ያለውን ሮማሪክ ዲንሆ አሞሱን ከኮትዲቫሩ አሴክ ሚሞሳ ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉ ሲሆን ወሳኙ አማካይ ሀብታሙ ተከስተን ጨምሮ አምስት ተጫዋቾች ደግሞ ክለቡን ሲለቁ በአንፃሩ ዳግም አወቀ ብሩክ አማኑኤል ፣ አሚር ሙደሲር እና አቤል እያዩ በበኩላቸው ኮንትራታቸውን ማራዘም የቻሉ ነባሮቹ ተጫዋቾች ሆነዋል።

በአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ እና ረዳቶቹ እየተመሩ ከነሀሴ 18/2018 ጀምሮ በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሲሰሩ የቆዩት አፄዎቹ በተለያዩ የጂም እና የሜዳ ተግባራት ዝግጅታቸው በመስራት ያሳለፉ ሲሆን የቡድናቸው ግንባታም ምን እንደሚመስል ለመገምገም የወዳጅነት ጨዋታዎች በማድረግ አዳማ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስን በተመሳሳይ 2ለ1 ሲያሸንፉ ከመቻል እና ሸገር ከተማ ጋር ደግሞ 1ለ1 በመለያየት ዝግጅታቸውን አገባደው የፕሪምየር ሊጉን የመክፈቻ መርሀግብር የፊታችን ቅዳሜ ወደ ሀላባ በማምራት ወላይታ ድቻን በመግጠም የውድድር ዘመኑን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...