የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ኢትዮጵያ ቡና የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ አብይ ካሳሁን ሊጉን ቢጀምሩም አሰልጣኙ በውጤት እጦት ካሰናበቱ በኋላ በጊዜያዊ አሰልጣኙ ሐይሉ አድማሱ በመጨረሻም ዋና አሰልጣኝ ሽመው በሳምሶን አየለ አመቱን ቢጨርስም በውጤት ረገድ ግን ወጣ ገባ ጉዞን እያሳለፈ ማጠናቀቅ ችሏል። አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በሁለት አመት ውል በአመቱ አጋማሽ መሾሙ ለተመለከተ ሁሉ በያዝነውም አመት ከክለቡ ጋር አብረው እንደሚቀጥሉ መገመት ቢቻልም ቡድኑ ባለፈው አመት አጋማሽ እንዳደረገው የአመራር ለውጥ ሁሉ የአሰልጣኝ ቡድኑ ላይ ለውጥ ማድረግን ምርጫው አድርጓል። በ2018 ከሊጉ የ38 ሳምንታት ጉዞው 13 በማሸነፍ 13 በመሸነፍ 12 የአቻ ውጤቶችን በመያዝ 40 ጎል በማስቆጠር 39 በማስተናገድ በ1 ንፁህ ጎል 51 ነጥቦችን ሰብስቦ 8ተኛ ደረጃንም ክለቡ በመያዝ አመቱን ቋጭቷል።
ለ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንድ አመት ከስድስት ወራት ውል ከነበራቸው አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት በመለያየት የሊጉን የልምድ ባለቤቱን አሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌን ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ቀጥሮ የጀመረው ቡድኑ በአሰልጣኙ ፍላጎትም በረዳት አሰልጣኝነት አምጣቸው ሐይሌ እና ለይኩን ታደሰን በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ደግሞ አምባዬ በፍቃዱን ቀጥሮ በዝውውሩ ላይ የነቃ ተሳተፉን በማድረግ 11 አዳዲስ ፈራሚዎችን በእጁ አስገብቷል።
ክለቡ ያስፈረማቸውን አዳዲስ ተጫዋቾችን ስንመለከት ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራን ከኢትዮጵያ መድን ፣ ተከላካዩ በረከት ወልደዮሐንስን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ የመስመር አጥቂው ዳዊት ገብሬን ከወልዋሎ ፣ አጥቂው ዳንኤል ዳርጌን ከምድረገነት ሽረ ፣ አማካዩ ሀብታሙ ተከስተን ከፋሲል ከነማ ፣ የግራ ተከላካዩ አብዱሰላም የሱፍን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ ሁለገቡን ተጫዋች ድልአዲስ ገብሬን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ የግራ ተከላካዩ ጳውሎስ ከንቲባን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ግብ ጠባቂው መኮንን መርዶክዮስን ከጋሞ ጨንቻ ፣ የወቅቱ የሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አጥቂው ታይባ ሞቦኒዮዋሚንን ከሀገሩ ክለብ ፕሪንስስ እና አማካዩ ጁኒየር ማቩንጎን ከሀገሩ ኮንጎ ክለብ ሴንት ሉፓፖ ለቡናማዎቹ የፈረሙ ተጫዋቾ ሲሆኑ ናይጄሪያዊው አማካይ ዲቫይን ዋቹኩዋ ፣ ይታገሱ ታሪኩ ፣ ኤርሚያስ ሹምበዛ ፣ አማኑኤል አድማሱ እና ረጂብ ሚፍታህ ደግሞ ኮንትራታቸው ሲራዘም ዳላንድ ኢብራሂምን ጨምሮ ወደ ሰባት የሚደርሱ ነባር ተጫዋቾችም ክለቡን መልቀቅ ችለዋል።
ከነሀሴ 18/2018 አንስቶ መቀመጫቸውን በአዳማ ከተማ በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሲሰሩ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ እና ረዳቶቻቸው በመታገዝ የጂም እና የሜዳ ተግባራትን በዝግጅት ወቅት እየሰሩ የከረሙ ሲሆን በወዳጅነት ጨዋታም ባህርዳር ከተማን 2ለ1 ፤ ወላይታ ድቻን ደግሞ 1ለ0 ሲያሸንፉ በሸገር ከተማ የ2ለ1 ሽንፈትን ደግሞ አስተናግደዋል። በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለ ጎል ሲቋጩ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በአንፃሩ 1ለ1 መለያየት የፈችለው የጋምቤላውን ባሮ ደግሞ 5ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን የፊታችን ዕሁድ በሜዳው አዲስ አበባ ስታዲየም ሸገር ከተማን በመግጠም የውድድር አመት ጉዞውን በይፋ ይጀምራል።
አስተያየት ይስጡ