መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የክለቦች ዝግጅት | ሀድያ ሆሳዕና
ሀዲያ ሆሳዕናቅድመ ውድድር ዝግጅትዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ሀድያ ሆሳዕና

አጋራ
አጋራ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ሀድያ ሆሳዕና የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

የ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከረዳት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ሽግግር ባደረገው አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ እየተመራ አመቱን ያሳለፈው ሀድያ ሆሳዕና ሁለት የውድድር መልኮችን በሊጉ እያሳየ በመጨረሻም አመቱን ከደረጃ ሰንጠረዡ የታችኛው ቦታን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል። ቡድኑ በሊጉ ከተደረጉ የ38 ሳምንታት ጉዟቸው 11 ጨዋታን በማሸነፍ 15 የአቻ ውጤቶችን በማስመዝገብ 12 ሽንፈቶችን በማስተናገድ 31 ጎሎችን በማስቆጠር 35 ግቦችን በተቃራኒው በማስተናገድ በ4 የጎል ዕዳ 48 ነጥብን በመያዝ 12ተኛ ደረጃን ይዘው የውድድር አመቱን ማገባደድ ችለዋል።

ለ2019 የሊጉ ውድድር ቡድኑ በክረምቱ አስቀድሞ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የተለያዩትን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በዋና አሰልጣኝነት በመቅጠር ረዳት አሰልጣኝ ሳይሾም አዳም ባዘዘውን በግብ ጠባቂ አሰልጣኝነት ቦታ ቀጥሮ በተጫዋቾች የዝውውር ገበያው ላይ የነቃ ተሳትፎን በማድረግ 13 አዳዲስ ፈራሚዎችን በእጁ አስገብቷል። ተከላካዩ ወንድማገኝ ማዕረግን ከሀዋሳ ከተማ ፣ አጥቂው ቢኒያም ጌታቸውን ከኢትዮጵያ ቡና ፣ አጥቂው ብርሀኑ አዳሙን ከመቐለ 70 እንደርታ ፣ አማካዩ ያሬድ ታደሰን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ የመስመር አጥቂው እዮብ ገብረማርያምን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ አማካዩ ጃዕፋር ሙደሲርን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ የመስመር ተከላካዩ ቶሎሳ ንጉሴን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አማካዩ አብዲ ዋበላን ከመቐለ 70 እንደርታ የመስመር አጥቂው ዳግም ደሳለኝ እና የመስመር ተከላካዩ ሄኖክ ደሳለኝ ከሆሳዕናው ያሆዴ ዋንጫ ውድድር ሲፈርሙ ከውጪ ሀገር ደግሞ ጋናዊውን ተከላካይ ፕሪንስ ባዱን ከአሻንቲ ኮቶኮ ፣ ናይጄሪያዊውን ተከላካይ አፎሊያ ፒተርስን ከኢንዩምባ እና ጋናዊውን አጥቂ ሳሙኤል ቦአቲንግን ከባንግላዲሹ ሞሀመዳን ዳካ ክለብ በይፋ መቀላቀል ችለዋል።

ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ ሔኖክ አርፊጮ ፣ ዳግም ወንድሙ ፣ ጄይላን ከማል ፣ ተፈራ አንለይ ፣ ደስታ ዋሚሾ ፣ አሸናፊ ኤልያስ ፣ ሱራፌል ተመስገን ፣ ታሪኩ ፀደቀ ፣ እንዳለ አባይነህ ፣ ናትናኤል ሞገስ እና ጋናዊው የግብ ዘብ እድሪሱ አውሱ ለተጨማሪ አመት ውላቸውን ለክለቁ ያደሱ 11 ተጫዋቾች ሲሆኑ ሁለት ወጣት ተጫዋቾች በበኩላቸው ወደ ዋናው ቡድን ማደግ ችለዋል።

በአዲሱ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ አጋፋሪነት ከነሀሴ 18/2018 አንስቶ በክለቡ መቀመጫ በሆነችው ሆሳዕና ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በጂም እና በሜዳ ስራዎች ቡድናቸውን ሲገነቡ የቆዩት ነብሮቹ የዝግጅት ምዕራፋቸውን በአምስት የወዳጅነት ጨዋታዎች በመፈተሽ ለሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ተዘጋጅተዋል። በሸገር ከተማ 2ለ1 በሀላባ ከተማ 1ለ0 ሲሸነፉ ጋሞ ጨንቻን 1ለ0 የሀድያ ሌሞ ወረዳን 2ለ0 እና የሀድያ ሆሳዕናን ከ20 አመት በታች ቡድንን 3ለ2 ማሸነፍ የቻሏቸው ጨዋታዎች ሲሆኑ የፊታችን ዕሁድም በሜዳቸው አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም ከአመታቶች በኋላ ባህርዳር ከተማን በሊጉ የመክፈቻ መርሀግብር የሚያስተናግዱም ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...