ደሴ ከተማ አሰልጣኝ ይልቃል ይታየውን ሾሟል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፍራው መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ከጫፍ ደርሶ የነበረው ደሴ ከተማ ለቀጣዩ የ2019 የውድድር ዘመን አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል።
አሰልጣኝ ይልቃል ይታየው ደግሞ አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል። የቀድሞው የዳሽን ቢራ ረዳት አሰልጣኝ የኒያላ እና በአዲስ ከተማ ክፍለከ ተማ ደግሞ ዘለግ ያሉ አመታትን ያሳለፈው አሰልጣኙ ደሴ ከተማን ለአንድ አመት መረከባቸው ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ