የኢትዮጵያ ከ20አመት በታች ብሄራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታ አድርገዋል።
ከሱዳን እና ሴኔጋል ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ መርሀግብር ከፊቱ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በታንዛኒያ በሚደረገው የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተካፋይ በሆነው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን መካከል በተደረገው የወዳጅነት ጨዋታ በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 3ለ0 ማሸነፍ ችሏል።
በኳስ ቁጥጥሩ እና ወደ ግብ በመድረሱ ተሽለው ለታዩት ዋልያዎቹ ከዕረፍት በፊት ዳዋ ሆቴሳ እና ፍፁም ጥላሁን ከዕረፍት በኋላ ደግሞ እዮብ ገብረማርያም ጎሎችን አስቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን በጥሩ የኳስ ፍሰት ወደፊት ተስቦ ለመጫወት የሚያደርጉት ጥረት ጥሩ ቢሆንም የመጨረሻው የሜዳ ክፍል ላይ ግን ያለመረጋጋቶች የአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ቡድን ነበረበት።

ይህንን የወዳጅነት ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ እና አዲሱ የስራ አስፈፃሚ እጩ አቶ አበባው ሠለሞን ፣ የሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ ተመስገን ዳና እና አንጋፋው አጥቂ ጌታነህ ከበደ በስፍራው በመገኘት ተመልክተውታል። ይህንን ጨዋታ በርካታ የእግር ኳስ ወዳድ ማህበረሰብ ለመገኘት በስታዲየሙ ቢገኝም ገብተው መመልከት እንዳይችሉም ተደርጓል።
አስተያየት ይስጡ