መነሻ ገጽ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በርካታ ዝውውሮችን ፈፅሟል
ኢትዮ-ኤሌክትሪክዜናዎችየኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በርካታ ዝውውሮችን ፈፅሟል

አጋራ
አጋራ

ኢትዮ ኤሌክሪክ የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም እና የዘጠኝ ነባሮችን ውል አራዝሟል።

በአሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ መሪነት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው እና በነሀሴ ወር መጀመሪያ ወደ ዝግጅት የሚገባው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአሰልጣኘሰ ኤርሚያስ ዱባለን ውል ለሁለት ተጨማሪ አመት ሲያራዝም አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ የዘጠኝ ነባር ተጫዋቾችን ውል ደግሞ ማራዘሙን ክለቡ ለሃትሪክ ስፖርት በላከልን መረጃ ለመመልከት ችለናል።

የቀድሞው የንግድ ባንክ እና ሀዋሳ ከተማ አማካይ ሲሳይ ገብረዋህድን ጨምሮ መሠረት ወርቅነት የመስመር ተከላካይ ከንግድ ባንክ ፣ አበባየው ጣሰው ግብ ጠባቂ ከመቻል ፣ ቤተልሄም መንተሎ አማካይ ከመቻል ፣ ሚቴ ረታ ግብ ጠባቂ ከልደታ ፣ ረድኤት ክንዴ የተከላካይ አማካይ ከልደታ ፣ ሚለን ጋየን አማካይ ከቦሌ ፣ ሂሩት ተስፋዬ የተከላካይ አማካይ ከንግድ ባንክ ፣ ታሪኬ ጴጥሮስ አጥቂ ከሀዋሳ ከተማ እና የመስመር ተከላካዩዋ ለምለም አሰታጥቄ  ከሀዋሳ ከተማ ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲሶቹ ፈራሚ ተጫዋቾች ሆነዋል።

ውላቸውን ያራዘሙ ዘጠኙን ተጫዋቾች ስንመለከት ፀጋነሽ ወራና አጥቂ ፣ ትዕግሥት ያደታ አማካይ ፣ ንግስቲ መአዛ ግብ ጠባቂ ፣ ቤተልሄም በቀለ ተከላካይ ፣ ባንቺይርጋ ተስፋዬ ተከላካይ ፣ ገብሬላ አበበ አማካይ ፣ ብርሀን ሀይለስላሴ አጥቂ ፣ ህዳት ካሱ አጥቂ እና እየሩስ ወንድሙ አጥቂ ናቸው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...