መነሻ ገጽ ዜናዎች የሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ
ዜናዎችየሴቶች ከፍተኛ ሊግየሴቶች ፕሪምየር ሊግየኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ

የሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን አከናወነ

አጋራ
አጋራ

ከተመሠረተ ወደ አራተኛ አመቱ የተጠጋው የኢትዮጵያ ሴት እግር ኳስ የሙያ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በአዳማ አድርጓል።

በ2015 አመተ ምህረት ምስረታውን ያደረገው እና በአሁኑም ሰዓት በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር በመልካ አዳማ ሆቴል አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን የማህበሩ አባላት እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በአዳማ ከተማ በዛሬው ዕለት ተደርጓል። የሙያ ማህበሩ ፕሬዝዳንት አሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ያስጀምሩት ይህ ጉባኤ በመቀጠል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ተወካይ ኢንስትራክተር በሀይሏ ዘለቀ እና የሲቪክ ማህበራት ባለስልጣን አቶ እንዳሻው በየተራ ስለ ማህበሩ ሃሳባቸውን መስጠት የቻሉ ሲሆን በተለይ ሌሎች የስፖርት ማህበር ተቋቁመው ብዙም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በማይታይበት በዚህ ወቅት በአጭር ጊዜ ተመስርቶ በርካታ ለውጥን እያመጣ የሚገኘው ይህ ማህበር ከፍ ያለ ድርሻ ስለተወጣ ሊበረታታ እንደሚገባው ተጠቁሟል።

በመቀጠል የ2018 ዕቅድ አፈፃፀም ፣ የአመቱ ክንውን እና የፋይናንስ ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የ2019 ዕቅድም በዝርዝር በጉባኤው ላይ መቅረብ የቻለ ሲሆን ከተሳታፊዎች ሀሳብ ከተሰጠ በኋላ በመጨረሻም ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እና የሚዲያ ባለሙያዎች የዕውቅና ስነ ስርዓት ተደርጎ ጉባኤው በመጨረሻም መቋጫውን አግኝቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...