የመስመር አጥቂው በነፃ ዝውውር ለተቀላቀለበት ክለብ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈጣን ከሚባሉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የመስመር አጥቂው አስቻለው ግርማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል። በወቅቱ በአንደኛ ሊጉ ተካፋይ በነበረው የአሰልጣኝ ፓውሎስ ጌታቸው ማንጎው ሱሉልታ ከተማ አስደናቂ ብቃቱን በማሳዩ በኢትዮጵያ ቡና በፕሪምየር ሊግ የተመለከትነው ተጫዋቹ በመቀጠል በሀዋሳ ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ከተጫወተ በኋላ ዘለግ ላሉ ጊዜያት ከእግር ኳሱ ርቆ ከቆየ በኋላ በነፃ ዝውውር ምድረገነት ሽረን በመቀላቀል ዛሬ ክለቡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እያደረገ በነበረው ጨዋታ 88ኛው ደቂቃ ዳንኤል ዳርጌን ተክቶ በመግባት ወደ ሊጉ በይፋ ተመልሷል።
አስተያየት ይስጡ