የኢትዮጵያ የሴት እግር ኳስ አሰልጣኞች ማህበር ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጋር በቅንጅት የሰጡት ስልጠና ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች ማህበር እና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የጋራ ትብብር ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታና የእውቀት ልውውጥ የስልጠና መርሀግብር በመልካ አዳማ ሆቴል በአዳማ ከተማ ሲደረግ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ፍፃሜውን አግኝቷል። በትላንትናው ዕለት ጅምሩን ባደረገው ይህ የስልጠና መርሀግብር በመጀመሪያው ቀን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በአሰልጣኝ ማዕደር እንየው ስለ (Periodization preseason and Tactics) እንዴት ሊታቀድና ሊተገበር ይችላል በሚለው ርዕስ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን የሙያ ማህበሩ አባላትም በአምስት ርዕሶች ላይ በግሩፕ በመሆን ውይይትና የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ተደርጓል።

በዛሬው የመዝጊያ ቀንም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በአሰልጣኝ ሀብታሙ ዳዲ (Soccer game management) በሚል ሰፋ ባለ ርዕስ ስልጠናው መሰጠት የቻለ ሲሆን ከስልጠናው መጠናቀቅም በኋላ ሰፊ የውይይት እና የመከራከሪያ ሀሳቦች ተሰንዝረው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዘለግ ያሉ ውይይቶች ተከናውኖ ጉባኤው የሁለት ቀናት ስልጠናውን ዛሬ ቋጭቷል።

አስተያየት ይስጡ