መነሻ ገጽ ዜናዎች የሴቶች እግር ኳስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ዛሬ ተጀመረ
ዜናዎችየሴቶች ከፍተኛ ሊግየሴቶች ፕሪምየር ሊግ

የሴቶች እግር ኳስ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ዛሬ ተጀመረ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ሴት እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በጋራ በመሆን ያዘጋጀው የአቅም ግንባታና የዕውቀት ልውውጥ ስልጠና ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአካዳሚው የስፖርት ባለሙያዎች ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃኸኝ አበራ የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ስለ አካዳሚው የስኬት ጉዞዎች አጭር ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናው የተሳካና ውጤታማ እንዲሆን በመመኘት ማስጀመር የቻሉ ሲሆን በመቀጠልም የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኞች የሙያ ማህበር ፕሬዝዳንት አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና አካዳሚው ከሙያ ማህበሩ ጋር አብሮ ለመስራትና የአቅም ግንባታና ዕውቀት ልውውጥ መድረክ በማዘጋጀቱ አመስግነው ከስልጠናው በቂ ዕውቀትን ለመውሰድ መዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅና ስፖርት አካዳሚው ለሀገራችን እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ በማድነቅና በማመስገን ስልጠናው የተቃና እውቀት የሚሸመትበት እንዲሆን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ተወካይ ኢንስትራክተር በሀይሏ በበኩላቸው የሙያ ማህበሩን እንቅስቃሴን አድንቀው በመቀጠል የስፖርት አካዳሚው ምርታማ ዜጋን በመፍጠር ያለው ሚና በመግለፅ አመስግነው የሙያ ማህበሩንም ለዚህ የእውቀት ሽግግር ዝግጁነት አመሥግነዋል።

በመጨረሻም ስልጠናው በአዳማ ከተማ መልካ አዳማ ሆቴል መጀመር የቻለ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ የሁለት ቀን ቆይታም ይኖረዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...