መነሻ ገጽ አርሲ ነገሌ የቡናማዎቹ እና የነገሌ አርሲው ተጫዋቾች ካምፕ ለቀው ወደ አሜሪካ አመሩ
አርሲ ነገሌኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቡናማዎቹ እና የነገሌ አርሲው ተጫዋቾች ካምፕ ለቀው ወደ አሜሪካ አመሩ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ቡናው አማካይ እና የነገሌ አርሲው አጥቂ የክለባቸውን ካምፕ ለቀው ወደ አሜሪካ አመሩ።

በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ከ2010 ጀምሮ ከታዳጊ ቡድን እግር ኳስን የጀመረው እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን ደግሞ ከ2014 ጀምሮ እስከ 2017 የውድድር ዘመን ድረስ ቆይታን ማድረግ የቻለው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አላዛር ሳሙኤል ባለፈው ክረምት የዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት አመት ውል መቀላቀሉ ይታወሳል። ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቀሪ የውል ዘመን ያለው ይህ ተጫዋች ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሳያሳውቅ ከካምፕ በመውጣት ወደ ሲያትል አሜሪካ ማምራቱን ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል። ተጫዋቹ በቀጣዮቹ ቀናት የጥገኝነት ጥያቄ ለማቅረብ ማሰቡንም ጭምር ሰምቻለሁ።

ሌላኛው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን የተገኘው እና በክለቡም በዋናው ቡድን በተከታታይ አራት አመታት ቆይታን ማድረግ የቻለው አጥቂው ዳግማዊ አርአያ ባለፈው የክረምቱ የዝውውር መስኮት ለአዲስ አዳጊው ክለብ ነገሌ አርሲ በመፈረም በፕሪምየር ሊጉ ከክለቡ ጋር ቆይታን ሲያደርግ የነበረ ቢሆንም ክለቡ ሳያውቅ ቀሪ ውል እያለው የክለቡን ሆቴል ለቆ ወደ አሜሪካ ማምራቱን አረጋግጫለሁ።

በዚህ አመት በተመሳሳይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቅሎ የነበረው አማካዩ አብርሀም ጌታቸው በአጋማሹ ወደ አሜሪካ ማምራቱም ይታወሳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...