መነሻ ገጽ ወላይታ ድቻ ወላይታ ዲቻ አዲስ ስራ አስኪያጅ ሾሟል
ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ወላይታ ዲቻ አዲስ ስራ አስኪያጅ ሾሟል

አጋራ
አጋራ

የቀድሞው የቦዲቲ ከተማ ስራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሰብሳቢ ኮሚቴው አዲሱ የጦና ንቦቹ ስራ አስኪያጅ በመሆን ተሹሟል።

በውጤት እጦት መነሻነት አቶ አሰፋ ሆሲሶን ከስራ አስኪያጅነት ካሰናበተ በኋላ በጊዜያዊ ስራ አስኪያጁ ምትኩ ሐይሌ ሲመራ የነበረው ወላይታ ድቻ ውጤታማ ጉዞው ለማስቀጠል በማሰብ አቶ ዋሲሁን ወልደዮሃንስን ዛሬ የክለቡ አዲስ ስራ አስኪያጅ በማድረግ በይፋ መሾማቸውን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጣለች።

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በስፖርት ሳይንስ እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የቋጩት ​አዲሱ ስራ አስኪያጅ የቦዲቲ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ በ2017 እና 2018 የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ እንዲሁም በ2018 ላይ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕርሚየር ሊግ ኮሚቴ በመሆን አገልግለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...