መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ድል ሲመለስ አርባምንጭ እና ኢትዮጵያ መድን ነጥብ ተጋርተዋል
ቅዱስ ጊዮርጊስባህርዳር ከተማአርባምንጭ ከተማኢትዮጵያ መድህንዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

በ ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ድል ሲመለስ አርባምንጭ እና ኢትዮጵያ መድን ነጥብ ተጋርተዋል

አጋራ
አጋራ

ሸገር ከተማን ከገጠመበት ስብስብ አምስት ተጨዋቾች መቀየር የቻሉት ፈረሰኛዎቹ የጣና ሞገዶቹን ሶስት ለ አንድ አሸነፉ

ባህር ዳር ከተማ 1-3 ቅዱስ ጊዮርጊስ

ጨዋታው በጀመረ በ 2ተኛ ደቂቃ የባህርዳር ከተማ ግብ ጠባቂ የሆነው ይገርማል መኳንንት የሰራውን ጠፋት በመጠቀም ተገኑ ያሻገረለት ኳስ አቤል ያል በአስደናቂ አጨራረስ ማስቆጠር ችሏል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስዎች ጫና በመፍጠር ሁለተኛ ጎል አቤል ያለው 26 ደቂቃ የተከላካዮችን ስህተት በመጠቀም ማስቆጠር ችሏል ።

በጨዋታው ብልጫ ተወስዶባቸው የነበሩት ባህርዳሮች በ 32 ደቂቃ በረከት ጥጋቡ ከ ሳጥን ውጭ አክርሮ በመታው ኳስ ሁለት ለ አንድ መሆን የቻሉ ቢሆንም እረፍት ሊወጡ ሽርፍራፊ ሰከንዶች ሲቀሩት አዲሱ አቱላ ከ ሀብታሙ ጉላላት የተቀበለውን ኳስ ከ እርቀት በረኛው መውጣቱን ተመልክቶ አክርሮ በመምታት ማስቆጠር ችሏል ።

በሁለተኛ አጋማሽ ከመጀመሪያው አጋማሽ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስሶች በመጀመሪያ አጋማሽ የገኙትን ነጥብ አስጠብቀው ለመጫወት ሲሞክሩ ተስተውሏል ።

የእለቱ ሁለተኛ በሆነው ጨዋታ አዞዎቹ ከ አምና ሻምፒዮዎቹ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል !!

ኢትዮጵያ መድን 0-0 አርባምንጭ ከተማ

በሁለቱም ቡድኖች በኩል የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ የተደረገበት ጨወታ ሲሆን ጨዋታው ያለግብ ባዶ ለባዶ መጠናቀቅ ችሏል

በጨዋታው የኢትዮጵያ መድን ተጨዋች የሆነው ረመዳን የሱፍ ለጎል የቀረበ ሙከራ ካደረገበት አጋጣሚ ውጪ በመጀመሪያው አጋማሽ የተለየ ሙከራ ያልተደረገ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ በተመሳሳይ ቀዝቃዛ እንቅስቃሴ ተደርጎበታል በሁለተኛው አጋማሽ አርባምንጭ ይሁን እንዳሻውን በ ሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የተወገደባቸው ቢሆን ከ ሻምፒናዎቹ ነጥብ መጋራት ችለዋል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...