መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ “ወደ አሜሪካ በምናደርገው ጉዞ ምንም ወጪ የለብንም” አቶ ባህሩ ጥላሁን (የኢ.እ.ፌ ዋና ስራ አስፈፃሚ)
ዋልያዎቹዜናዎች

“ወደ አሜሪካ በምናደርገው ጉዞ ምንም ወጪ የለብንም” አቶ ባህሩ ጥላሁን (የኢ.እ.ፌ ዋና ስራ አስፈፃሚ)

አጋራ
አጋራ

በአሜሪካ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት የሚያደርገው የዋልያዎቹ ስብስብ ሀገር ውስጥ ለሚያደርገው ዝግጅት ከሚያወጣው ወጪ ውጪ በሚጓዙበት ወቅት የአውሮፕላን እና አሜሪካ ከተጓዙ በኋላ ያሉ የተለያዩ ወጪዎቹን ዲሲ ዩናይትድ የሚሸፍን ይሆናል ።

በዛሬው እለት በጁፒተር ሆቴል የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ መግለጫ  ሰጥተዋል ።

አቶ ባህሩ ስለ አሜሪካው ጉዞ እና ፌዴሬሽኑ ስለሚያገኛቸው ጥቅማ ጥቅም የገለፁ ሲሆን ዋሊያዎቹ በስፍራው ስለተገኙ ብቻ 25 ሺህ ዶላር የሚያገኙ ሲሆን በተጨማሪም ጨዋታውን ማሸነፍ ከቻሉ 50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ ይሄም ገቢ ኢትዮጵያ ከ ግብፅ ጋር ካደረገችበች ጨዋታ በኋላ የሚገባ ከፍተኛ ገቢ እንደሚሆን ገልፀዋል።

በነገው ዕለት ወደ አሜሪካ የሚያቀናው ልዑካን ቡድን ሀያ ተጨዋቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ ሰላሳ አንድ አባላት እንደሚጓዙ ገልፀዋል።

የዋሊያዎቹ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስለምርጫው ምርጫውን ቀድምን ነበር ያደረግነው ሁሉም ተጨዋቾች በግላቸው ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለፁ ሲሆን የመጀመሪያ ዕቅድ ቢበላሽ ብዬ የያዝኳቸውን ተጨዋቾች ነው ወደ ሰብስቤ ያካተትኩት ብለዋል።

የዋልያዎቹን ጨዋታ ለመታደም ወደ 12 ሺህ የሚጠጋ ደጋፊ እስካሁን ቲኬት መቁረጡም የተገለፀ ሲሆን ጨዋታውም የፊታችን ቅዳሜ የሚደረግ ይሆናል።

ዋሊያዎቹ በጨዋታው በማክሮን ትጥቅ አምራች ድርጅት የተመረተውን አዲስ ማልያ በጨዋታው እንደሚጠቀሙ አቶ ባህሩ ጥላሁን ገልፀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...