መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን አምስት ተጨዋቾች ሲያስፈርም የአንድ ተጨዋቾች ውል አራዝሟል ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክዜናዎችየኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን አምስት ተጨዋቾች ሲያስፈርም የአንድ ተጨዋቾች ውል አራዝሟል ።

አጋራ
አጋራ

በትላንትናው እለት ህክምናቸውን በመጨረስ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  በመቅረብ ፍርማቸውን ካስቀመጡ መካከል የመጀመሪያዋ ምርቃት ፈለቀ ስትሆን ምርቃት በ ዘንድሮ የውድድር ዓመት በአንደኛው ዙር በግሏ ለአርባምንጭ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ስታደርግ የነበረች ሲሆን በሁለተኛ ዙር ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረደው ቂርቆስ ክ / ከተማን መቀላቀል ችላለች ። ምርቃት በ ብርሀኑ ግዛ ቡድን ለሁለት ዓመት ለመቆየት በወር ያልተጣራ ወራዊ ደሞዝ 204,310.00 ፍርማዋን አኑራለች ።

ሁለተኛ ፈራሚዋ ሰላማዊት ጎሳዬ በሀዋሳ ከተማ በተለይም በዘንድሮ ዓመት የንግድ ባንክ ከፍተኛ ተፎካካሪ በነበርው ቡድን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ስታደርግ የነበረች የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቾች ስትሆን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመት በንግድ ባንክ ለመቆየት በወር 204,310.00 ያልተጣራ የሚከፈላት ይሆናል ።

በተመሳሳይ ሁለቱ የ ሀዋሳ ከተማ ጥንካሬ የነበሩት እፀገነት ግርማ እሙሽ ዳንኤል በ 2018 ዓ.ም በ ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተፎካካሪ ለማድረግ በሁለት  ዓመት ውል አምርተዋል እያንዳዳቸውም ያልተጣራ 238,793 ብር የሚከፈላቸው ይሆናል ።

ሌላኛዋ የ ንግድ ባንክን የተከላካይ ስፍራ ለማጠናከር ፍርማዋን ያኖረችው ቤቴልሄም ግዛቸው ስትሆን በሴካፋ ዞን አሸናፊዎቹ ቤት ለሁለት ዓመት በወር ያልተጣራ ወራዊ ደሞዝ 195,689.00 የሚከፈላት ይሆናል ።

የቡድኑ አምበል የናሽናል ቲሙ የረዥም ጊዜ ግብ ጠባቂ ከንግድ ባንክ ጋር በርካታ ዋንጫዎችን ከፍ አድርጋ ማንሳት የቻለችው ታሪኳ በርገነ በድጋሚ በንግድ ባንክ ማለያ ለመድመቅ  ለሁለት ዓመት በወር ያልተጣራ  ደሞዝ 214,931.00 እየተከፈላት ለመጫወት ፍርማዋን አኑራለች

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...