መነሻ ገጽ ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና የመቶ ሺ ብር ቅጣት እንዲከፍል ሲወሰን አስር ተጫዋቾች የጨዋታ እገዳ እና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

ኢትዮጵያ ቡና የመቶ ሺ ብር ቅጣት እንዲከፍል ሲወሰን አስር ተጫዋቾች የጨዋታ እገዳ እና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል

አጋራ
አጋራ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. አስቻለው ታመነ (መቻል): ክለቡ ከሃዋሳ ከተማ ጋር ባደረገው የ32ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 40 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

2. ወንድሜነህ ደረጄ (ባህርዳር ከተማ) : ክለቡ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ባደረገው የ32ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 64 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ) እና በተቁ 2 መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

3. አለን ካይዋ (ኢትዮጵያ መድን ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ መድን
  2. ኢትዮጵያ መድን – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  3. ኢትዮጵያ ቡና – ኢትዮጵያ መድን
  4. ኢትዮጵያ መድን – ሲዳማ ቡና

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

4. መስፍን ታፈሰ (ሲዳማ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. ሲዳማ ቡና – ኢትዮጵያ መድን
  2. ሲዳማ ቡና – ኢትዮጵያ ቡና
  3. አርባምንጭ ከተማ – ሲዳማ ቡና
  4. ሲዳማ ቡና – ባህርዳር ከተማ
  5. ኢትዮጵያ መድን – ሲዳማ ቡና

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

5. ኬኔዲ ከበደ (ወላይታ ድቻ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. ወላይታ ድቻ – ኢትዮጵያ ቡና
  2. ቅዱስ ጊዮርጊስ – ወላይታ ድቻ
  3. ሲዳማ ቡና – ወላይታ ድቻ
  4. ወላይታ ድቻ – መቻል
  5. ወላይታ ድቻ – ኢትዮ ኤሌትሪክ

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

6. ሽመክት ጉግሳ (ኢትዮ ኤሌትሪክ ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. ኢትዮ ኤሌትሪክ – ወላይታ ድቻ
  2. ኢትዮ ኤሌትሪክ – ሀዲያ ሆሳዕና
  3. አርባምንጭ ከተማ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
  4. ኢትዮ ኤሌትሪክ-ሲዳማ ቡና
  5. ወላይታ ድቻ – ኢትዮ ኤሌትሪክ

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ‥ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

7. ራምኬል ጀምስ (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. ኢትዮጵያ ቡና – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
  2. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ኢትዮጵያ ቡና
  3. መቻል – ኢትዮጵያ ቡና
  4. ኢትዮጵያ ቡና – ሲዳማ ቡና
  5. ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ – ኢትዮጵያ ቡና

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

8. ኪቲካ ጅማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. ባህርዳር ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  2. አርባምንጭ ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  3. ፋሲል ከነማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  4. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ድሬደዋ ከተማ

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

9. አቤል አሰበ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  2. ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ መድን
  3. ሀዲያ ሆሳዕና – ድሬደዋ ከተማ
  4. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ድሬደዋ ከተማ

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

10. አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : ከታች በተጠቀሱት 10 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።

  1. አርባምንጭ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
  2. ድሬደዋ ከተማ – አዳማ ከተማ
  3. ሃዋሳ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
  4. ድሬደዋ ከተማ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
  5. ባህርዳር ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
  6. ድሬደዋ ከተማ – ፋሲል ከነማ
  7. ቅዱስ ጊዮርጊስ – ድሬደዋ ከተማ
  8. አዳማ ከተማ – ድሬደዋ ከተማ
  9. ሀዲያ ሆሳዕና – ድሬደዋ ከተማ
  10. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ድሬደዋ ከተማ

በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እ∶ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 2 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ

ቅጣት ብር 2000 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።

11. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር በነበረው የ32ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንትን ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበርን እና የኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝን በስም በመጥራት አፀያፊ ስድብ ስለመኣደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል ።

ስለሆነም የከለቡ ደጋፊዎች ላጠፉት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 4(ሀ) ብር100 000 /አንድ መቶ ሺህ/እንዲከፍል የውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...