መነሻ ገጽ ዜናዎች ብሩክ ባይሳ እና ፋሃድ አዚዝ የጨዋታ እገዳ ሲጣልባቸው እንዲሁም ከክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቅጣት ተላልፎበታል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ብሩክ ባይሳ እና ፋሃድ አዚዝ የጨዋታ እገዳ ሲጣልባቸው እንዲሁም ከክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቅጣት ተላልፎበታል

አጋራ
አጋራ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ብሩክ ባይሳ (አርባምንጭ ከተማ): ሐሙስ ሚያዝያ 2 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 85 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

2. ፋሃድ አዚዝ (ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ) : ሰኞ መጋቢት 29 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 69 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የ ውድድርአመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

 

3. ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከባህር ዳር ከተማጋር በነበረው የ24ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ግጥሚያው 3 ደቂቃ ዘግይቶ ለመጀመሩ ምክኒያት እንደነበረ ሪፖርት ቀርቦበታል ።

በመሆኑም በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል 1 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 13.2 ተቁ 17 መሰረት ከለቡ ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...