መነሻ ገጽ ዜናዎች የክለቦች ክፍያ አስተዳደር ስርዓት መመሪያን ባለመተግበር በአራት ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ።
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የክለቦች ክፍያ አስተዳደር ስርዓት መመሪያን ባለመተግበር በአራት ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ።

አጋራ
አጋራ

በክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ መሰረት ክለቦች የየወሩን ጥቅል የደመወዝ ሪፖርት ወር በገባ እስከ 10 ቀን ማሳወቅ እንዳለባቸው ተጠቅሷል።     መመሪያው ከሚያዘው ውጪ የፕሪሚየር ሊጉ አራት ክለቦች ሪፖርት ማድረግ ከነበረባቸው ከ12 እስከ 27 ቀናት በላይ በመቆየት ሪፖርት አድርገዋል።

የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ በክለቦች የክፍያ ስርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 01/2016 አንቀፅ 9 መሰረት በአራት ክለቦች ላይ የቅጣት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህ መሰረትም :-

ሀዋሳ ከተማ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ12 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 70,000(ሰባ ሺህ ብር)

አዳማ ከተማ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ23 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 180,000(አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር)

አርባምንጭ ከተማ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ24 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 190,000(አንድ መቶ ዘጠና ሺህ ብር) እንዲሁም

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረግ ከነበረበት ከ27 ቀናት በላይ በመዘግየቱ ብር 220,000(ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ብር) ተቀጥተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...