መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢኒያም በላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተለያይቷል ! በቀጣይስ ወዴት ሊያመራ ይችላል … ?
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ቢኒያም በላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተለያይቷል ! በቀጣይስ ወዴት ሊያመራ ይችላል … ?

አጋራ
አጋራ

ያለፉትን ሁለት ያክል አመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበረዉ እና ከክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማሳካት ችሎ የነበረዉ ቢኒያም በላይ በመጨረሻም ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል።

በ2009 መጨረሻ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በመልቀቅ ወደ ጀርመን አምርቶ የሙከራ ጊዜን ማሳለፍ ችሎ የነበረዉ እና ወደ አልባኒያዊው ክለብ ስከንደርቡ በማምራት ከክለቡ ጋር የሊጉን የዋንጫ ክብር ማሳካት ችሎ የነበረዉ ፤ በመቀጠል ወደ ስዊዲን በማቅናት ለስሪያንስካ እና ኡሚያ ክለቦች ተጫዉቶ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ለሲዳማ ቡና ፣ መቻል እና ያለፉትን ሁለት ያክል አመታት ደግሞ በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ ማድረግ የቻለዉ የመስመር ተጫዋቹ ቢኒያም በላይ በመጨረሻም ከክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መለያየቱን አስታውቋል።

በይፋ ከክለቡ ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ያሰፈረዉ ቢኒያም በቀጣይ ቀናት ቀጣይ ማረፊያዉ ይታወቃል ተብሎ ሲጠበቅ ፤ ፋሲል ከነማ እና የቀድሞ ክለቦቹ መቻል እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተጫዋቹን ፊርማ ለማግኘት ንግግር ላይ መሆናቸዉም ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...