መነሻ ገጽ ዜናዎች የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ መጋቢት 23 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አራት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 17 ጎሎች ተቆጥረዋል። አንድ ጨዋታ(የባህር ዳር ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ) በተጫዋች አለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል። 19 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ የተመዘገበ ቀይ ካርድ የለም።

በሳምንቱ በስድስት ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። በረከት ግዛው(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ብሩክ ሙሉጌታ(ኢትዮጵያ መድን)፣ በረከት ሳሙኤል (ሃዋሳ ከተማ)፣  ቢንያም አይተን(አዳማ ከተማ) እና አማኑኤል ኤረቦ(ቅዱስ ጊዮርጊስ) በሳምንቱ ጨዋታ አምስተኛ የጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ሲወሰን ማይክል ኔልሰን /ሻሸመኔ ከተማ – ተጫዋች/ ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር በነበረው  ጨዋታ ከዳኛውና ከረዳት ዳኞች እይታ ዉጪ የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋችን ገፍትሮ ከጣለው በኋላ እግሩን ረግጦት የሄደ መሆኑን ሪፖርት በመደረጉ በፈጸመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት 4/አራት ጨዋታ እንዲታገድና ብር /3000/ ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...