መነሻ ገጽ ዜናዎች የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ታህሳስ 01 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች ስድስት በመሸናነፍ ቀሪ አንዱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 16 ጎሎች በ14  ተጫዋቾች ተቆጥሯል። 28 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ ሁለት ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።

 

በተጫዋች እና ቡድን አመራሮች ላይ በተላለፈ ውሳኔ ኦላኒ ሴቄታ(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን መሪ) ክለባቸው ከ ሻሸመኔ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በ73 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ ፤ ዳግም ንጉሴ(ሀዲያ ሆሳዕና) ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው ጨዋታ በ 90+2 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ እንዲሁም ቴዎድሮስ በቀለ /ሀምበሪቾ-ተጫዋች/ ክለቡ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ያልተመዘገቡ ተጫዋቾች ከተቀመጡበት ቦታ ላይ ሆኖ የውሀ መጠጫ ፕላስቲክ ወደ ሜዳ ስለመወርወሩ ሪፖርት ቀርቦበት ተጫዋቹ በፈጸመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ብር 25 000 /ሀያ አምስት ሺህ / እንዲከፍል ተወስኗል።

በተጨማሪም ለአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ/ሀዋሳ ከተማ-ዋና አሰልጣኝ/ እና አሰልጣኝ ደግያረጋል ይግዛው(ባህር ዳር ከተማ) የፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ለማነጋገር ጥሪ አድርጓል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...