የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ታህሳስ 08 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች ሰባት በመሸናነፍ ቀሪ አንዱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 23 ጎሎች በ21 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 43 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ ሶስት ቀይ ካርድ(በሁለተኛ ቢጫ) ተመዝግቧል ።
በሳምንቱ አራት ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። ሱሌማን ሀሚድ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ ሲሞን ፒተር(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ወንድሜነህ ደረጄ(ኢትዮጵያ ቡና) በሳምንቱ ጨዋታዎች ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ሲሆን ተጫዋቾቹ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ እንዱሁም ሚሊዮን ሰለሞን(ሃዋሳ ከተማ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከተ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ተወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -
በአራት ክለቦች ላይም በተጫዋቾች ካርድ ምክንያት የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ ተላልፏል። ከሀምበሪቾ አቤል ከበደ፣ ቶሎሳ ንጉሤ፣ ምንታምር መለሰ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና ፀጋሰው ዴማሙ የተባሉ አምስት ተጫዋቾች፥ ከኢትዮጵያ መድን ኦሊሴማ ቺኔዱ፣ ንጋቱ ገ/ስላሴ፣ ሙሴ ከበላ፣ ያሬድ ካሳዬ፣ ተመስገን ዮሃንስ እና ያሬድ ዳርዛ የተባሉ ስድስት ተጫዋቾች፥ ከሀዲያ ሆሳዕና ብሩክ ማርቆስ፣ ኩሊባሊ ካድር፣ ተመስገን ብርሃኑ፣ ቃለአብ ውብሸት እና ሰመረ ሀፍተይ የተባሉ አምስት ተጫዋቾች ፥ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሱሌማን ሀሚድ፣ ኪቲካ ጅማ፣ ብሩክ እንዳለ፣ ሲሞን ፒተር ፣ ሱሌማን ሀሚድ እና ሲሞን ፒተር የተባሉ ስድስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ክለቦቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡