የቀድሞ አሰልጣኛቸዉን ስዩም ከበደን በማሰናበት በምክትል አሰልጣኙ አረጋዊ ወንድሙ እየተመሩ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች አዲስ አሰልጣኝ ሾመዋል።
ሲዳማ ቡናዎች አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራዉ (ሞሪኒዮን) የክለባቸዉ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ በአንድ ዓመት ኮንትራት ያስፈረሙ ሲሆን አሰልጣኙ በዛሬው እለት በክለቡ ፅህፈት ቤት በመገኘት የኮንትራት ዉል ተፈራርሟል።
ሲዳማ ቡና በዘንድሮዉ የዉድድር ዓመት እስካሁን ካደረጋቸዉ 8 ጨዋታዎች 8 ነጥብ በመሰብሰብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።