በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መቐለ ላይ መቐለ ከተማ ና ጅማ አባጅፋር ተገናኝተው ባለሜዳው መቐለ ከተማ ያሬድ ከበደ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1-0 ማሸነፍ ችሏል።
የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ብልጫ መውሰድ የቻሉት መቐለ ከተማዎች ግብ ለማስቆጠር 12 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የፈጀባቸው። ከአማኒኤል ገብረሚካኤል የተሻገረለትን ኳስ ያሬድ ከበደ በ12ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ወደ ግብነት ቀይሮታል። ከግቡ መቆጠር በኀላ ብዙም ማራኪ እንቅስቃሴ ሳይስተዋልበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
ከእረፍት መልስ ግቡን ለመቀልበስ ተጭነው የተጫወቱት ጅማ አባጅፋሮች በተሻለ የኳስ ቁጥጥርና በተደጋጋሚ ወደ መቐለ ከተማ ግብ ክልል መድረስ ቢችሉም በእለቱ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየውን የመቐለ ከተማ ግብ ጠባቂ ፍሊፕ ኦቦኖ ማለፍ ተስኗቸው ለመሸነፍ ተገደዋል።