የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ታህሳስ 01 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች ስድስት በመሸናነፍ ቀሪ አንዱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 16 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ተቆጥሯል። 28 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ ሁለት ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።
በተጫዋች እና ቡድን አመራሮች ላይ በተላለፈ ውሳኔ ኦላኒ ሴቄታ(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን መሪ) ክለባቸው ከ ሻሸመኔ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ በ73 ኛ ደቂቃ ላይ ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 10000 /አስር ሺ/ እንዲከፍሉ ፤ ዳግም ንጉሴ(ሀዲያ ሆሳዕና) ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው ጨዋታ በ 90+2 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ እንዲሁም ቴዎድሮስ በቀለ /ሀምበሪቾ-ተጫዋች/ ክለቡ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ያልተመዘገቡ ተጫዋቾች ከተቀመጡበት ቦታ ላይ ሆኖ የውሀ መጠጫ ፕላስቲክ ወደ ሜዳ ስለመወርወሩ ሪፖርት ቀርቦበት ተጫዋቹ በፈጸመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ብር 25 000 /ሀያ አምስት ሺህ / እንዲከፍል ተወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
በተጨማሪም ለአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ/ሀዋሳ ከተማ-ዋና አሰልጣኝ/ እና አሰልጣኝ ደግያረጋል ይግዛው(ባህር ዳር ከተማ) የፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ለማነጋገር ጥሪ አድርጓል።