መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ በድንቅ ግስጋሴያቸው ቀጥለዋል
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ በድንቅ ግስጋሴያቸው ቀጥለዋል

አጋራ
አጋራ

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ከ9 ሰዓት ጀምሮ በወልቂጤ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል የተደረገው ጨዋታ በተከታታይ ጨዋታዎች በምርጥ ብቃት ላይ በሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች 4 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል ።

ወልቂጤ ከተማዎች በ11ኛ ሳምንት ጨዋታ በመከላከያ በተሸነፉበት ጨዋታ ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ሶሰት ቅያሪዎችን ያደረጉ ዳግም ንጉሴ ፣ ረመዳን የሱፍ እና በሀይሉ ተሻገርን በተስፋዬ ነጋሽ ፣ አበባው ቡጣቆ እና ፋሲል አበባየሁ ምትክ ጨዋታውን የጀመሩ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊሶች ባህርዳር ከተማን ከረቱበት ጨዋታ አንድ ቅያሪ ብቻ በማድረግ በከነአን ማርክነህ በረከት ወልዴን በማሰለፍ ጨዋታውን ጀምረዋል ።

የቅዱስ ጊዮርጊሶች የበላይነት በታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታ ጥሩ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን ያስመለከተ ነበር ። ከመሀል ክፍል ወደ አጥቂ መስመር በሚላኩ ተደጋጋሚ ኳሶች የፈረሰኞቹ ተጨዋቾች ክትፎዎቹን መፈተን የቻሉባቸውን አጋጣሚዎች መፍጠር ችለዋል ።

በጨዋታው የነበረው የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ 9ኛ ደቂቃ ላይ በረመዳን የሱፍ ከርቀት ወደ ግብ የተመታው ኳስ የነበረው ሲሆን የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግብ ጠባቂ ቻርለስ ሉክዋጎ ኳሱን ወደ ውጪ አውጥቶታል ።

16ኛው ደቂቃ ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የግብ ክልል በረጅም የተነሳው ኳስ በአጥቂው እስማኤል ኦሮ ኦጎሮ አማካኝነት ወደ ግብ ተቀይሯል ። አቤል ያለው ከያብስራ ተስፋዬ የደረሰውን ኳስ በሳጥን ውስጥ ሆኖ ወደ ግብ ሞክሮት በግብ ጠባቂው ሰይድ ሀብታሙ ቢመለስም በቅርብ የነበረው ኦሮ አጎሮ አስቆጥሮ ፈረሰኞቹን መሪ አደረገ ።

ከአንድ ደቂቃ በኋላ ጋቶች ፓኖም በቀኝ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ለኦጎሮ ቀንሶለት የነበረ ቢሆንም ለግቡ በጣም በቅርበት እና ነፃ ሆኖ የነበረው አጥቂ የመታው ኳስ የግቡን ቋሚ መትቶ ሊወጣ ችሏል ። ከግቡ በኋላ በተደጋጋሚ የወልቂጤ ከተማን ተከላካይ ክፍል በመፈተን ላይ የነበሩች ፈረሰኞቹ 22ኛ ደቂቃ ላይ የፍፁም ቅጣት ምት ማግኘት ችለዋል ።

ኦጎሮ በረጅም የተላከለተን ኳስ በሳጥን ውሰጥ ሆኖ ለማስቆጠር በሚሞክርበት ጊዜ ከኋላው የነበረው የወልቂጤ ከተማው ተጫዋች ዮናስ በርታ ጥፋት የሰራበት ሲሆን ጥፋቱን የሰራው ተጫዋች በቀጥታ የቀይ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አማኑኤል ገብረሚካኤል ደግሞ የፍፁም ቅጣት ምቱን ማስቆጠር ችሏል።

በሁለት ግብ ልዩነት በመመራት ላይ የነበሩት ወልቂጤ ከተማዎች በተወሰነ መልኩ ቀድሞ ከነበረው በተሻለ ለመንቀሳቀስ ችለው ነበር ። የመጀመሪያው አጋማሽም ሌላ ግብ ሳያስተናግድ በፈረሰኞቹ የሁለት ለዜሮ መሪነት ተጠናቀቀ ።

በሁለተኛው አጋማሽ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ኳሱን በመቆጣጠር ወልቂጤ ከተማዎች ደግሞ የሚገኙ አጋጣሚዎችን በፍጥነት ወደ ፊት መስመር በመውሰድ ለመጫወት ጥረቶች ያደረጉበች የነበረ ቢሆንም እስከ ሁለተኛው ውሀ እረፍት ድረስ በሁለቱም በኩል ይህ ነው የሚባል የግብ ሙከራ አልተደረገም ነበር ።

74ኛ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ ለገባው ለቡልቻ ሹራ በረጅም የተላከውን ኳስ ሰይድ ሀብታሙ ወጥቶ ለማውጣት ሲሞክር ኳሱን ያገኘው አማኑኤል ገብረሚካኤል በፍጥነት ወደ ግብ ቢሞክረውም የወልቂጤ ከተማ ተከላካይ ፈጥኖ ደርሶ ኳሱን ግብ ከመሆን ታድጎታል ። ከደቂቃዎች በኋላም ሱሌማን ሀሚድ ከቀኝ መስመር በመነሳት ወደ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በግራ አሰግሩ አክርሮ የመታው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ወደ ወቷል ። በድጋሚ ከአስር ደቂቃዎች በኋላ ራሱ ከመሰመር ይዞ የገባውን ኳስ አክርሮ በመምታት የፈረሰኞቹን መሪነት ወደ 3 ለ 0 ከፍ አደረገ ።

ተቀይሮ በገባው ተገኑ ተሾመ ላይ በሳጥን ውስጥ ጥፋት ተሰርቶበት ፈረሰኞቹ ያገኙትን የጨዋታው ሁለተኛ የፍፁም ቅጣት ምት ቡልቻ ሹራ ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በመጨረሻም ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ወልቂጤ ከተማ 0 ሆኖ ጨዋታው ተጠናቋል ።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 26 በማድረስ መሪነቱን ሲያሰፋ ወልቂጤ ከተማ በበኩሉ በ16 ነጥብ ወደ 10ኛ ደረጃ ተንሸራቷል ።

በ13ኛ ሳምንት ወልቂጤ ከተማ ሲዳማ ቡናን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ሀድያ ሆሳዕናንን የሚገጥሙ ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...