መነሻ ገጽ ከ 20 ዓመት በታች የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት ተካሂዷል
ከ 20 ዓመት በታችዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት ተካሂዷል

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ታዳጊ ወጣቶች ፕሪምየር ሊግ የ2014 የውድድር ዓመት የዕጣ ማውጣት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል ። በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው መርሀ ግብር በመቀጠልም የ2013 አጠቃላይ ሪፖርት በውድድር ባለሙያ ወ/ሪት ምህረት ጉታ ፣ የዳኞች ሪፖርት በዳኞች ባለሙያ አቶ ሙሉጌታ ምስጋናው ፣ የህክምና ሪፖርት በህክምና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል የሺዋስ እንዲሁም የቴክኒክ እና ልማት ዳይሬክቶሬት እቅድ በአቶ እንዳለየሱስ አባተ አማካኝነት ቀርቧል።

ከሻይ እረፍት በኋላ በ2014 የደንብ ውይይት እና አጠቃላይ በውድድሩ ዙርያ አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በሚመለከታቸው አካላትም ምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቶባቸው የ2014 ደንብ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል ። በመቀጠልም የውድድሩ ምድቦች ፣ የጨዋታ መርሀ ግብሮች እና ውድድሮች የሚካሄዱበት ስፍራ ዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሂዷል ።

በዕጣው መሰረት የምድብ ሀ ጨዋታዎች በጎንደር ከተማ የምድብ ለ ደግሞ በአሰላ ከተማ የሚካሄዱ ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታዎች የካቲት 12/2014 ዓ.ም የሚካሄዱ ይሆናል ።

ምድብ ሀ ( ጎንደር )
1. ሀላባ ከተማ
2. ሲዳማ ቡና
3. ሰበታ ከተማ
4. ሀድያ ሆሳዕና
5. ባህርዳር ከተማ
6. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
7. ወላይታ ድቻ
8. አርባምንጭ ከተማ
9. አዳማ ከተማ
10. ኢትዮ ኤሌክትሪክ

ምድብ ለ ( አሰላ )
1. አዲስ አበባ ከተማ
2. ወላይታ ዞን
3. ሀዋሳ ከተማ
4. ድሬዳዋ ከተማ
5. ቅዱስ ጊዮርጊስ
6. መከላከያ
7. ኢትዮጵያ መድህን
8. ኢትዮጵያ ቡና
9. ፋሲል ከተማ

የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች
ምድብ 1
ሀላባ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ሲዳማ ቡና ከ አዳማ ከተማ
ሰበታ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
ሀድያ ሆሳዕና ከ ወላይታ ድቻ
ባህርዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ምድብ 2
ወላይታ ዞን ከ ፋሲል ከተማ
ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ
ኢትዮጵያ መድን ከ ድሬዳዋ ከተማ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...