መነሻ ገጽ Caf confederation cup ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ የአፍሪካ መድረክ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል
Caf confederation cupቅዱስ ጊዮርጊስባህርዳር ከተማዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ የአፍሪካ መድረክ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል

አጋራ
አጋራ

 

የ2023/24 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅደመ ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆኗል ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በተደረገው ድልድል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዛንዚባሩ “KMKM” ሲደለደል ባህርዳር ከተማ በበኩሉ ከታንዛኒያው አዛም ጋር ተደልድሏል ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ሲያደርግ ፤ በደርሶ መልስ የሁለተኛውን ዙር ከተቀላቀለ የ2022/23 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ከሆነው አል አህሊ ጋር ይጫወታል ።

ባህር ዳር ከተማ በበኩሉ የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው የሚያደርግ ሲሆን ፤ በደርሶ መልስ የሁለተኛውን ዙር ከተቀላቀለ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካ ጋር ይጫወታል ።

የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከነሀሴ 12 – ነሀሴ 14 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከነሀሴ 19 – 21 ባሉት ቀናት መካከል ይደረጋሉ ።

በተጨማሪም የሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ቀዳሚ ጨዋታዎች ደግሞ ከመስከረም 2 – 4 የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከመስከረም 18 – 20 ባሉት ቀናት መካከል ይደረጋሉ ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...