የ2023/24 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅደመ ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆኗል ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ በተደረገው ድልድል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዛንዚባሩ “KMKM” ሲደለደል ባህርዳር ከተማ በበኩሉ ከታንዛኒያው አዛም ጋር ተደልድሏል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ሲያደርግ ፤ በደርሶ መልስ የሁለተኛውን ዙር ከተቀላቀለ የ2022/23 የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ ከሆነው አል አህሊ ጋር ይጫወታል ።
- ማሰታውቂያ -
ባህር ዳር ከተማ በበኩሉ የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው የሚያደርግ ሲሆን ፤ በደርሶ መልስ የሁለተኛውን ዙር ከተቀላቀለ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካ ጋር ይጫወታል ።
የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ከነሀሴ 12 – ነሀሴ 14 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከነሀሴ 19 – 21 ባሉት ቀናት መካከል ይደረጋሉ ።
በተጨማሪም የሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ቀዳሚ ጨዋታዎች ደግሞ ከመስከረም 2 – 4 የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ከመስከረም 18 – 20 ባሉት ቀናት መካከል ይደረጋሉ ።