ትላንት አላዛር ማርቆስን ማስፈረማቸዉን ይፋ ያደረጉት የጣና ሞገዶቹ ዛሬ ደግሞ የሌላኛዉን ግብ ጠባቂያቸዉን ይገርማል መኳንንትን ኮንትራት ማራዘማቸዉን ይፋ አድርገዋል።
ተጫዋቹ በባህርዳር ከነማ ሁለት አመታቶችን ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በቀጣይ የዉድድር አመትም ከክለቡ ጋር እንደሚቀጥል ተረጋግጧል፤ ባህርዳር ከነማ በቀጣይ ስብስቡን ለማጠናከር አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ጥረት እያደረገ እንደሆነ ተሰምቷል።