መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛው ወራጅ ክለብ የሚለይበት ወሳኝ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአርባምንጭ ከተማወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ከፕሪሚየር ሊጉ ሶስተኛው ወራጅ ክለብ የሚለይበት ወሳኝ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

አጋራ
አጋራ

የ2015 ዓ/ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ የ30ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመደረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ዛሬም ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚወርደዉ ሶስተኛዉ ክለብ የሚለይበት ወሳኝ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰአት ይደረጋሉ።

ከዚህ በፊት ቀሪ ጨዋታዎች እያሏቸው በጊዜ ከሊጉ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ኢትዮ ኤሌትሪክ የተሰናበቱ ሲሆን እነሱን ተከትሎ ከሊጉ ላለመዉረድ በርካታ ክለቦች ትንቅንቅ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን በስተመጨረሻም ላለመዉረድ የሚደረገዉ ትንቅንቅ ዉስጥ ወልቂጤ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ቀርተዋል።

በሊጉ ዉስጥ ቀሪ አንድ አንድ ጨዋታ ብቻ እየቀራቸዉ ወልቂጤ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ በ34 ነጥብ እና በ33 ነጥብ የደረጃዉ ሰንጠረዥ ግርጌ 13ኛ ደረጃ ላይ እና 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ከሁለቱ ክለብ አንዱ ወደ ከፍተኛ ሊግ ወራጅ የሚሆን ሲሆን ጨዋታቸውን ዛሬ በተመሳሳይ ሰአት የሚያደርጉ ይሆናል።

በዚህም መሰረት ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰአት አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ ጋር በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስታዲየም ጨዋታዉን የሚያደርግ ሲሆን እንዲሁም በእዛው ሰአት ወልቂጤ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ጋር በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታዉን የሚያደርጉ ይሆናል።

የዛሬዉን ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች የሚያሸንፉ ከሆነ ወልቂጤ ከተማ በ37 ነጥብ ሊጉ ዉስጥ መቆየቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን አርባምንጭ ከነማ በበኩሉ በ1 ነጥብ አንሶ በ36 ነጥብ ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚወርድ ይሆናል።

ይህ ለሁለቱም ክለቦች ወሳኝ የሆነዉ የመጨረሻው ጨዋታ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰአት ላይ የሚደረግ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...