መነሻ ገጽ ዜናዎች የ2015 ዓ/ም የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዉድድር በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት በዛሬው እለት በሀዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
ዜናዎች

የ2015 ዓ/ም የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዉድድር በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት በዛሬው እለት በሀዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

አጋራ
አጋራ

በስምንት ምድብ ተከፍሎ በ31 ክለቦች መሀከል የሚደረገው የ2015 ዓ/ም የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የእግርኳስ ኳስ ዉድድር ከሰኔ 14 እስከ ሀምሌ 8 የሚካሄድ ሲሆን በዛሬው እለት በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች መክፈቻዉን አግኝቷል።

የመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አዲሱ ቃሚሶ ፣ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አንበሴ አበበ እንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዉድድር ስነስርዓት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ የተገኙ ሲሆን የመክፈቻ ጨዋታ በምድብ ‘ሀ’ ዉስጥ በሚገኙት በ5ኛ ካምፕ እና በኩርሙክ ጉሌ መሀከል የተደረጉ ሲሆን ጨዋታዉን ኩርሙክ ጉሌ 3-1 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ የዉድድር ዘመኑን በአሸናፊነት ሲጀምር ከእሱ በማስከተል በእዛዉ ምድብ በሚገኙት በሚቶ ክለብ እና በቤሮ ወርቅ መሀከል ጨዋታ የተካሄደ ሲሆን ጨዋታዉን ሚቶ ክለብ 4-2 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ የዉድድር ዘመኑን በአሸናፊነት ጀምሯል።

ቀጣይ የምድብ ጨዋታዎች ነገ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እና በግብርና ኮሌጅ ቀጥለዉ የሚካሄዱ ይሆናል።

ምድብ “ለ” ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም

ቃላድ አምባ 3:00 መንጌ ቤላሻንጉል
ጎንደር አራዳ 5:00 ወንዶ ገነት

ምድብ “ሐ” ግብርና ኮሌጅ

ናቲ ዩኒቲ 3:00 ሡልልታ ቢ
ዋሊያ 5:00 ቡልቡላ አሜን

ምድብ “መ” ግብርና ኮሌጅ

አመያ 7:00 ዱል አዘሃቢ
ቦሌ ገርጂ 9:00 ገንዳ አብዲ ቦሩ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...