በስምንት ምድብ ተከፍሎ በ31 ክለቦች መሀከል የሚደረገው የ2015 ዓ/ም የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የእግርኳስ ኳስ ዉድድር ከሰኔ 14 እስከ ሀምሌ 8 የሚካሄድ ሲሆን በዛሬው እለት በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች መክፈቻዉን አግኝቷል።
የመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አዲሱ ቃሚሶ ፣ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አንበሴ አበበ እንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዉድድር ስነስርዓት ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ የተገኙ ሲሆን የመክፈቻ ጨዋታ በምድብ ‘ሀ’ ዉስጥ በሚገኙት በ5ኛ ካምፕ እና በኩርሙክ ጉሌ መሀከል የተደረጉ ሲሆን ጨዋታዉን ኩርሙክ ጉሌ 3-1 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ የዉድድር ዘመኑን በአሸናፊነት ሲጀምር ከእሱ በማስከተል በእዛዉ ምድብ በሚገኙት በሚቶ ክለብ እና በቤሮ ወርቅ መሀከል ጨዋታ የተካሄደ ሲሆን ጨዋታዉን ሚቶ ክለብ 4-2 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ የዉድድር ዘመኑን በአሸናፊነት ጀምሯል።
- ማሰታውቂያ -
ቀጣይ የምድብ ጨዋታዎች ነገ በሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እና በግብርና ኮሌጅ ቀጥለዉ የሚካሄዱ ይሆናል።
ምድብ “ለ” ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም
ቃላድ አምባ 3:00 መንጌ ቤላሻንጉል
ጎንደር አራዳ 5:00 ወንዶ ገነት
ምድብ “ሐ” ግብርና ኮሌጅ
ናቲ ዩኒቲ 3:00 ሡልልታ ቢ
ዋሊያ 5:00 ቡልቡላ አሜን
ምድብ “መ” ግብርና ኮሌጅ
አመያ 7:00 ዱል አዘሃቢ
ቦሌ ገርጂ 9:00 ገንዳ አብዲ ቦሩ