የ2015 ዓ/ም የኢትዮጵያ የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዉድድር በዛሬው እለት በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት በሀዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በሁለት ምድብ ተከፍሎ በዘጠኝ ክለቦች መሀከል የሚደረገዉ የኢትዮጵያ የሴቶች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የእግር ኳስ ዉድድር ዛሬ ጠዋት በተካሄደ አንድ ጨዋታ መክፈቻዉን አግኝቷል።
የመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አንበሴ አበበ ፣ የሀዋሳ ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ክፍሌ ዋሬ ፣ የሀዋሳ ከነማ እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ መኖሪያ ቡጣሻ እና የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን የመጀመሪያው ጨዋታ በምድብ “ሀ” ዉስጥ በሚገኙት በቢሾፍቱ ከተማ እና በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መሀከል የተደረገ ሲሆን ጨዋታዉን ቢሾፍቱ ከተማ 1-0 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ የዉድድር ዘመኑን በድል ጀምሯል።
- ማሰታውቂያ -
እንዲሁም በእዛዉ ምድብ የሚገኙት ኤግልስ ዲላ እና አምቦ ጎል ፕሮጀክት ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰአት በሀዋሳ አርተፊሻል ሜዳ ጨዋታቸዉን የሚያካሂዱ ይሆናል።
የ2015 ዓ/ም የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ዉድድር ላይ ከእየ ምድባቸዉ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ ክለቦች ወደ 2016 ዓ/ም የኢትዮጵያ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ የሚያልፉ ይሆናል።