By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Reading: ፋሲል ከነማና ውስጥ አዋቂው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዳግም ተጣመሩ
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
Š 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግፋሲል ከነማ

ፋሲል ከነማና ውስጥ አዋቂው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዳግም ተጣመሩ

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 3 years ago
Share
SHARE

👉ኢትዮጵያ ቡና ያቀረበው 350 ሺህ ብር ደመወዝ
ተቀባይነት አጥቷል

አጼዎቹ የንግስና ቦታቸውን ለማስመለስና በአፍሪካ መድረክ ጠንካራ ተፎካካሪ ክለብ ለመሆን በማለም
አሰልጣኝ ውበቱ አባተን አሰልጣኝ ለማድረግ ተስማሙ።

ዋሊያዎቹን ለአፍሪካና ለቻን ሻምፒዮና የማብቃት ታሪክ የሰሩት አሰልጣኝ ውበቱ በጠንካራ ሁኔታ ሲፈልጓቸው ከነበሩትና ሙያዊ ግልጋሎታቸውን ካገኙት ከፋሲል ከነማና ከኢትዮጵያ ቡና ተወካዮች ጋር ድርድር ሲያደርጉ ቆይተው ከፋሲል ከነማ ጋር ተስማምተዋል።

አሰልጣኙ በ2003 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ካደረጉት የኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሁለት ጊዜ የተደራደሩ ሲሆን ከክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ከአንድ የቦርድና ከደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ጋር የተደረገው ውይይት ያለ ስምምነት ተቋጭቷል። ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ 400 ሺህ ብር የወር ደመወዝ በሶስት አመት የሚከፈለው 14,400,000 ለሁለት ተካፍሎ 7,200,000 ሺህ ብር በቅድሚያ ክፍያ ተከፍሎት ግማሹ በ36 ወር ተካፍሎ በደመወዝ 200 ሺህ ብር እንዲከፈላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ ቀርቷል። በተለይ የቦርድ አባሉ አቶ ዳንኤል ገንዘቡ መብዛቱን በመግለፅ አቅሙ የለንም ለቦርድም አይቀርብም በማለታቸው ያለ ስምምነት ተለያይተዋል።

- ማሰታውቂያ -

ክለቡን የወከሉት ወገኖች ለሁለተኛ ጊዜ ድርድር ከመቀመጣቸው በፊት በአሰልጣኞቹ ወገን ሌላ የመደራደሪያ ሀሳብ ቀርቧል። በመጀመሪያ አመት የሚከፈለው የአንድ አመት ደመወዝ 4,733,000 በቅድሚያ ተከፍሎ ቀሪው ለሁለት አመት ለ24 ወር በደመወዝ እንዲከፈለው ቢጠይቅም የደጋፊ ማህበሩ አመራሮችና ቦርዱ ሳይስማሙ ቀርተዋል።

ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ቦርዱና የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ተወያይተው ክለቡ 300 ሺህ ብር ደጋፊ ማህበሩ 50 ሺህ ብሩን ሸፍነው 350 ሺህ ብር ለመክፈል ቢጠይቁም ለውሳኔ በመዘግየታቸውና አሰልጣኙን ማሳመን ሳይችሉ በመቅረታቸው ፊታቸውን ወደ ሌላ የውጪ ሀገር አሰልጣኝ ማዞራቸው ታውቋል።

ጠንካራ ድርድር ያደረጉትና አሰልጣኙን ለማሳመን ሽንጣቸውን ገትረው የተደራደሩት አጼዎቹ ፋሲል ከነማዎች በኢትዮጵያ ቡና በአርባ ምንጭና በድሬዳዋ ከተሞች ከንቲባዎች ሳይቀር የተፈለገውን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት አሰልጣኛቸው አድርገው መርጠዋል።

የ2013ና የ2014 ጠንካራ ተፎካካሪነቱን ያጣው ፋሲል ከነማ የጎንደር ከተማ ከንቲባና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢን አቶ ባዩ አቦሀይ ድርድሩን እንዲመሩ ያደርገው ጥረት በስምምነት መቋጨቱ ታውቋል። ከንቲባው ከዚህ ሀላፊነታቸው አስቀድሞ የፋሲል ከነማ ደጋፊ በመሆን ስታዲየም ተገኝተው ቡድኑን ያበረታቱ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ከንቲባው ለፋሲል ቅርብ መሆናቸው ለለውጥ ትልቅ ድጋፍ እንደሚሆን ይታመናል።

የክለቡ የውስጥ አዋቂ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አሰልጣኝ ውበቱ አስቀድሞ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ የመሆን እድል የነበራቸው ሲሆን በወቅቱ ሀላፊነት ላይ የነበሩትን አሰልጣኝ ሃይሉ ነጋሽ /ቲጋናን/ ለመጀመሪያ ጊዜ ምክትል አድርገው እንደሾሙ በመጥቀስ ምክትሌ አድርጌ አሁን ደግሞ በመንገዱ ላይ አልቆምም በማለት ጥያቄውን አለመቀበላቸው ይታወሳል።

ፋሲል ከነማዎች እስከ ሰኔ 30/2015 ድረስ ያለው የአሁኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ውል እስኪያልቅ ድረስ ውሉን ይፋ ባያደርጉትም በኢትዮጵያ ቡና የቀረበላቸውን 350 ሺህ ብር ያልተቀበሉትን አሰልጣኝ ውበቱ ከቀጣዮቹ ሶስት አመታት አጼዎቹን እንዲያሰለጥኑ ኢትዮጵያ ቡናዎች ካቀረቡት የተሻለ እስከ 400 ሺህ ብር አካባቢ እንዲከፈላቸው ሳይስማሙ እንዳልቀረም እየተነገረ ነው። በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሹመትና ዝርዝር ስምምነት ዙሪያ ከሁለቱም ወገኖች ይፋ የተደረገ መረጃ ባይኖርም የውል ስምምነታቸውን የሚገልጸው ሰነድ ባለፈው አርብ ፌዴሬሽን መግባቱን ከፌዴሬሽኑና ከክለቡ ታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ያስረዳል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በ250 ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ እየሰሩበት ከነበረው የዋሊያዎቹ ሀላፊነታቸው ለፌዴሬሽኑ ባስገቡት በስምምነት እንለያይ ጥያቄ በስምምነት ከተለያዩ በሳምንታት ውስጥ ከተሻለ የደመወዝ ክፍያ ጋር ጠንካራ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሀላፊነት ለመረከብ መስማማታቸው ታውቋል።

አሰልጣኙ ቡድኑን በደንብ እንዲያጠናክሩ የፈለጓቸውን ተጨዋቾች የማስቀረት ሌሎች ቡድኑን የሚያጠናክሩ ተጨዋቾችን እንዲያስፈርሙ ሞቅ ያለ የዝውውር በጀት እንደተመደበላቸው የታወቀ ሲሆን በዲሲፕሊን ላይ ድርድር የማያውቁት አሰልጣኝ ውበቱ መልበሻ ቤቱን የመቆጣጠርና የመምራት ሙሉ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ ፋሲል ከነማን በአንደኛው አመት ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚያደርጉ በሁለኛው አመት ወደ ሻምፒዮንነት እንዲመልሱ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሩ ተፎካካሪ እንደሚያደርጉ በእቅድ ደረጃ ማሳወቃቸው የወጣው መረጃ ያስረዳል።

ፈሲል ከነማዎች በ2013 በፕሪሚየር ሊጉ ላይ የነገሱ ሲሆን በ2014 ሁለተኛ ሆነው ጨርሰዋል ክለቡ በ2015 አሰልጣኝ ሃይሉ ነጋሽና አሰልጣኘ አሸናፊ በቀለን ቢሾምም በእስካሁኑ 28ኛ ሳምንት መርሀግብር በ39 ነጥብና 4 ግብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የፊታችን ዓርብ ሳምንት ሰኔ 23/2015 ደግሞ ከወረደው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር 29ኛ ሳምንት መርሀግብሩን ያካሂዳል።

ፋሲል ከነማ ቀጣዮቹን ሁለት ጨዋታዎችን ቢያሸንፍ እንኳ የሚደርሰው 45 ነጥብ ላይ በመሆኑ ከአራተኛነት የዘለለ ደረጃ እንደማይኖረው በመረጋገጡ የዝውውርና የሹመት ስራው ከአሁኑ ለቀጣዮቹ አመታት እየተዘጋጀ መሆኑን እንደሚያሳይ ከክለቡ ታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article FIFA and FIFPRO join forces to combat social media hate speec
Next Article የ2015 ዓ/ም የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዉድድር በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት በዛሬው እለት በሀዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ዋልያዎቹየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንዜናዎችThe BiG Interview

“በጣም ትንሽ ለሆነችው ሙከራዬ ከደጋፊው የተሰጠኝ ምላሽ መሸከም ከምችለው በላይ በመሆኑ ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ አልቅሻለሁ” ኢንስ. አብርሀም መብራቱ

Yishak belay By Yishak belay 6 years ago
ኢትዮጵያ ቡና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል !!
ሀትሪክ በቀጠሮዋ ቀን ነገ
    እንደልማድዎ ይጠብቋት….አሁንም ቀጠሮ አክባሪ ናት…
ሀድያ ሆሳዕና ምክትል አሰልጣኝ ሾመ !
​የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ 
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

Š Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?