መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ ካፍ ስታዲየሞቻችን ማገዱ ያስከተለው ከፍተኛ ወጪ….. ዋሊያዎቹ የፊታችን ማክሰኞ ከማላዊ አቻቸው ጋር ላለባቸው የመርሀ ግብር ማሟያ  ጨዋታ  ነገ  ወደ ሞዛምፒክ መዲና ማፑቶ ያቀናሉ…
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ካፍ ስታዲየሞቻችን ማገዱ ያስከተለው ከፍተኛ ወጪ….. ዋሊያዎቹ የፊታችን ማክሰኞ ከማላዊ አቻቸው ጋር ላለባቸው የመርሀ ግብር ማሟያ  ጨዋታ  ነገ  ወደ ሞዛምፒክ መዲና ማፑቶ ያቀናሉ…

አጋራ
አጋራ

ጨዋታው ሀገር ውስጥ አለመካሄዱን ተከትሎ ፌዴሬሽኑን ለከፍተኛ ወጪ መዳረጉን የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ባህሩ ጥላሁን ትላንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የብዙዎቹ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች በመንግስትና በተለያዩ  አካላት ድጋፍ እንደሚያገኙም ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸው ፌዴሬሽኑም በተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አብራርተዋል።

ለዛሬ ስታዲየሞቻችን ደረጃውን አላሟሉም በሚል በመታገዳቸውና ጨዋታዎቻችንን በሜዳችን  ማድረግ  ባለመቻላችን ይወጣል የተባለው ከፍተኛ ወጪን እናስቃኛችሁ…

*….ለሜዳው ኪራይ 8 ሺህ ዶላር

*….የአባላቱ የአውሮፕላን ጉዞ ወጪ 1.9 ሚሊዮን ብር

*…. ለሚቆዩበት ጊዜ የሆቴል ወጪ….

*….ወደ ሞዛምፒክ ለሚጓዙ ተጨዋቾች ለእያንዳንዳቸው
በቀን 100 ዶላር …በቡድን መሪነት ለሚሄዱ አመራሮች
ለእያንዳንዳቸው በቀን  200 ዶላር አበል….

*….ለዳኞቹና ኮሚሽነሩ የአውሮፕላንና የሆቴል ወጪ
ሙሉ ክፍያ….

ማስታወሻ:- የአውሮፕላን ጉዞ ወጪው ብቻ በብር ሲሆን
ሌላው በሙሉ በዶላር በመሆኑ ፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱን ማየት ይቻላል…..በሜዳችን ማድረግ ብንችል ከአርቢትሮቹ ክፍያ ውጪ ሌሎቹ ወጪዎች በብር መሆኑ ሲታሰብ ሀገር ውስጥ ባለመደረጉ ሀገሪቱን ለከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ እንደዳረጋት መረዳት ይቻላል…

አሁንም ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ ሜዳዎቹ የሚገኙባቸው ክልሎች፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና ባለሀብቶች በአጠቃላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንደ ሀገር የሚጠበቅባቸውን እንዲፈጽሙ አደራ እንላለን።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...