ጨዋታው ሀገር ውስጥ አለመካሄዱን ተከትሎ ፌዴሬሽኑን ለከፍተኛ ወጪ መዳረጉን የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ባህሩ ጥላሁን ትላንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የብዙዎቹ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች በመንግስትና በተለያዩ አካላት ድጋፍ እንደሚያገኙም ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸው ፌዴሬሽኑም በተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አብራርተዋል።
ለዛሬ ስታዲየሞቻችን ደረጃውን አላሟሉም በሚል በመታገዳቸውና ጨዋታዎቻችንን በሜዳችን ማድረግ ባለመቻላችን ይወጣል የተባለው ከፍተኛ ወጪን እናስቃኛችሁ…
*….ለሜዳው ኪራይ 8 ሺህ ዶላር
*….የአባላቱ የአውሮፕላን ጉዞ ወጪ 1.9 ሚሊዮን ብር
- ማሰታውቂያ -
*…. ለሚቆዩበት ጊዜ የሆቴል ወጪ….
*….ወደ ሞዛምፒክ ለሚጓዙ ተጨዋቾች ለእያንዳንዳቸው
በቀን 100 ዶላር …በቡድን መሪነት ለሚሄዱ አመራሮች
ለእያንዳንዳቸው በቀን 200 ዶላር አበል….
*….ለዳኞቹና ኮሚሽነሩ የአውሮፕላንና የሆቴል ወጪ
ሙሉ ክፍያ….
ማስታወሻ:- የአውሮፕላን ጉዞ ወጪው ብቻ በብር ሲሆን
ሌላው በሙሉ በዶላር በመሆኑ ፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱን ማየት ይቻላል…..በሜዳችን ማድረግ ብንችል ከአርቢትሮቹ ክፍያ ውጪ ሌሎቹ ወጪዎች በብር መሆኑ ሲታሰብ ሀገር ውስጥ ባለመደረጉ ሀገሪቱን ለከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ እንደዳረጋት መረዳት ይቻላል…
አሁንም ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ ሜዳዎቹ የሚገኙባቸው ክልሎች፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንና ባለሀብቶች በአጠቃላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንደ ሀገር የሚጠበቅባቸውን እንዲፈጽሙ አደራ እንላለን።