መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከነማ ከሊጉ መሪዉ ጋር ያለዉ የነጥብ ልዩነት የሰፋበትን ሽንፈት በሀዲያ ሆሳዕና አስተናግዷል።
ሀዲያ ሆሳዕናባህርዳር ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከነማ ከሊጉ መሪዉ ጋር ያለዉ የነጥብ ልዩነት የሰፋበትን ሽንፈት በሀዲያ ሆሳዕና አስተናግዷል።

አጋራ
አጋራ

ባህርዳር ከነማዎች ከሊጉ መሪ ጋር ያላቸዉ የነጥብ ልዩነት የሰፋበት እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕናዎች ደረጃቸዉን ከፍ ያደረጉበት ጨዋታ በከቤራዎቹ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የጨዋታዉ የመጀመሪያ ክፍለ ግዜ ፈጣን በሆነ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን ገና ከጅምሩ የባህርዳር ከነማዎቹ አጥቂ ሀብታሙ ታደሰ ያገኛት ኳስ በሀዲያ ሆሳዕናዎቹ በረኛ የተመለሰበት ወደ ጎል የመታት ኳስ ተጠቃሽ ናት።

የባህር ዳሮቹ ፉዓድ ፈረጃ በ6ኛዉ ደቂቃ ላይ ጉዳት አስተናግዶ በቻርልስ ሪቫኑ ተቀይሮ ከወጣ በኋላ የጨዋታ ብልጫዉ ወደ ሀዲያ ሆሳዕናዎች ያመራ ሲሆን ሠመረ ሀፍታይ በ29ኛዉ ደቂቃ ለሀዲያ ሆሳዕናዎች ኳሱን ከመረቡ አገናኝቶ ጨዋታዉ በሀዲያ ሆሳዕና 1-0 በሆነ መሪነት ቀጥሎ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

ጨዋታው ከእረፍት መልስ በ1-0 ዉጤት ለአምስት ደቂቃዎች ብቻ የቀጠለ ሲሆን ተመስገን ብርሀኑ ለሀዲያ ሆሳዕናዎች ኳሱን ከመረብ አገናኝቶ ጨዋታዉ በሀዲያ ሆሳዕናዎች 2-0 መሪነት የቀጠለ ቢሆንም 67ኛው ደቂቃ ላይ ቻርለስ ሪቫኑ ለባህርዳሮች ኳሱን ከመረብ አገናኝተ ጨዋታዉ ወደ 2-1 አምርቷል።

ባህርዳሮች ከግቧ በኋላ ሌላ ተጨማሪ ጎል ለመድገም ተጭነዉ መጫወትን ቀጥለዉ በተደጋጋሚ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና የግብ ክልል ማምራት የቻሉ ሲሆን በጨዋታዉ መገባደጃ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ በዱሬሳ ሹቢሳ በኩል ለጎል የቀረበ ኳስ አግኝተዉ የነበረ ቢሆንም ሳይጠቀሙበት ቀርተዉ ጨዋታዉ በሀዲያ ሆሳዕና 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በዚህም መሰረት ባህርዳር ከነማ ከመሪዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለዉ የነጥብ ልዩነት ወደ 5 አድጓል።

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...