መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አገባደዋል !!
ሀዋሳ ከተማሀዲያ ሆሳዕናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አገባደዋል !!

አጋራ
አጋራ

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ23ተኛ ሳምንት መርሐግብር ሶስተኛ ዕለት ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸዉን ያለ ግብ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

በእኩል ሰላሳ አንድ ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ ተቀምጠዉ የዕለቱ ጨዋታቸውን ለማከናወን ወደ ሜዳ በገቡት የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ቀዳሚ የሚያደርጋቸዉን ግብ ለማስቆጠር እና የጨዋታዉ የበላይ ለመሆን ሲጥሩ በጨዋታዉ መባቻ ላይም ሀድያዎች ጥሩ የግብ ዕድል መፍጠር ችለዉ ነበር ፤ በዚህም ተመስገን ብርሀኑ ከብርሀኑ በቀለ የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ መሐመድ ሙንታሪ ኳሷን ወደ ዉጭ አውጥቶታል።

የመጨረሻ ተከላካዮቹን የሜዳዉ መሐል ድረስ አስጠግቶ ይጫወት የነበረዉን ሀድያ ሆሳዕና ለማጥቃት ለፈጣን የመስመር አጥቂዎቻቸዉ በሚልኳቸዉ ረጃጅም ኳሶች በጨዋታዉ ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ የነበሩት ሀይቆቹ በኤርትራዊው አጥቂ አሊ ሱለይማን እና ሙጅብ አማካኝነት በአጋማሽ ጥሩ ጥሩ የግብ ዕድሎችን መፍጠር ሲችሉ ተስተውሏል።

በተለይ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች በቀሩበት ወቅትም ሀይቆቹ በአብዱልባሲጥ አማካኝነት ድንቅ ሙከራን ማድረግ ቢችሉም በግብ ጠባቂዉ ፔፔ ሰይዶ አማካኝነት ኳሷ ግብ ከመሆን ከሽፋለች።

ከዕረፍት መልስ የተወሰደባቸውን ብልጫ ለመመለስ በሚል በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ቀይረዉ ወደ ሜዳ ያስገቡት ሀይቆቹ ነገር ግን ባሰቡት ልክ ያን ያህል ጥሩ ሲንቀሳቀሱ አልተስተዋለም። በተቃራኒው በመጠኑም ቢሆን ጥሩ የሚባል የመሐል ሜዳ ብልጫ የነበራቸዉ ነብሮቹ በሁለተኛዉ አጋማሽም ኳስ እና መረብን ለማገናኘት እንዲሁም ተጠቃሽ ሙከራም ለማድረግ ሲቸገሩ ተስተውሏል።

በዚህ ሂድት የቀጠለዉ እና ያን ያህል እምብዛም በሙከራ ያልታጀበዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም በመደበኛዉ ዘጠና ደቂቃ እንዲሁም በጭማሪዉ አምስት ደቂቃም ግብ ስይቆጠርበት ጨዋታዉ 0ለ0 በሆነ አቻ ዉጤት ተገባዷል። ዉጤቱን ተከትሎም ሀዋሳ ከተማ በ32 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፤ በተመሳሳይ በዕለቱ ጨዋታ አንድ ነጥብ ያሳካዉ ሀድያ ሆሳዕናም በ32 ነጥብ በግብ ክፍያ ተሽሎ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...