መነሻ ገጽ አፍሪካ ዋንጫ « ኢትዮጵያን በደርሶ መልስ አሸንፈን ስድስት ነጥብ እንወስዳለን » ካባ ዲያዋራ
አፍሪካ ዋንጫአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዋልያዎቹዜናዎችጊኒ

« ኢትዮጵያን በደርሶ መልስ አሸንፈን ስድስት ነጥብ እንወስዳለን » ካባ ዲያዋራ

አጋራ
አጋራ

ለ2023 የኮት ዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በደርሶ መልስ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን የሚገጥመው የጊኒ ብሐራዊ ቡድን አሰልጣኝ ካባ ዲያዋራ በሞሮኮ የሚደረጉትን ሁለት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አሸንፈው ሙሉ ስድስት ነጥብ እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡

ማርች 24 እና ማርች 27 በሞሮኮ ከተሞች የሚደረጉትን ሁለት የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አስመልክተው ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ ያደረጉት አሰልጣኝ ዲያዋራ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በሚገባ እናውቀዋለን በምናውቃቸው መጠንም ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡

አሰልጣኙ ተጋጣሚያቸው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድንን አስመልክቶ ለተነሳላቸው ጥያቄ

« የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዘጠና በመቶ በላይ በሃገር ውስጥ ሊግ በሚጫወቱ ልጆች የተገነባ ብሔራዊ ቡድን ነው፤ የባለፈው የቻን ውድድር በደንብ እንድናያቸው ዕድል ፈጥሮልናል፣ ኳስ ይዘው መጫወት ይፈልጋሉ፣ ብዙ ይሮጣሉ፣ ሶስቱንም ጨዋታዎቻቸውን ተመልክተን ለነሱ የሚሆን ታክቲክ አዘጋጅተናል፤ ሁለቱንም ጨዋታዎች አሸንፈን ስድስት ነጥብ ከኢትዮጵያ ላይ ወስደን ወደኮት ዲቯር እናቀናለን፡፡»

የሁለቱ ሃገራት ጨዋታዎች በማርች 24 በካዛብላንካ መሃመድ አምስተኛ እንዲሁም የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ማርች 27 በራባት ከተማ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ይደረጋሉ፡፡

ከሜዳቸው ውጪ መጫወታቸው በውጤቱ ላይ ልዩነት ይፈጥር እንደሆነ የተጠየቁት አሰልጣኙ ሲመልሱ

« ሞሮኮን የመረጡት ሁለቱም ፌዴሬሽኖች በስምምነት ነው፤ ወቅቱ የራማዳን ጾም ወቅት በመሆኑ ለኛም በመሃል ጉዞ ሳናደርግ መጫወታችን ይጠቅመናል የትራንስፖርት ወጪም ይቀንሳል፤ በርካታ ጊኔያውያን በሞሮኮ እንደሞኖራቸው በኛ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖራል ብዬ አላስብም ዋናው ነገር በርካታ ጊኒያውያውያን በስታዲየም ተገኝተው ጨዋታውን እንዲመለከቱ መጋበዙ ላይ ነው፡፡»

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...