በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቅዱስ ጊዮርጊስና መከላከያ ጨዋታ የገባ ግብ ሽረዋል የተባሉት ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤል የስድስት ወር ዕገዳ ተጣለባቸው።
ከትላንት በስቲያ እሁድ ሁለቱ ቡድኖች ያረጉት ጨዋታ 0ለዐ ነተጠናቀቀ ሲሆን የፈረሰኞቹ ፍሪምፖንግ ሜንሱ በጭንቅላት ያስቆጠራትና መስመር ያለፈች ኳስ ብትሆንም አርቢትሮቹ ሳያጸድቋት መቅረቱ በፈረሰኞቹ ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱ ይታወሳል።
የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ከጨዋታው ኮሚሽነር አዲሱ ነጋሽ የቀረበለትን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ሁለቱ አርቢትሮችን ጥፋተኛ ሆነው በማግኘቱ ዕገዳውን ማስተላለፉ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ