መነሻ ገጽ አፍሪካ “በላይቤሪያ ቆይታዬ የተደሰትኩት ኢንስትራክተሮቹ ለመንግስቱ ወርቁ በሰጡት ክብር ነው” ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
አፍሪካካፍዜናዎች

“በላይቤሪያ ቆይታዬ የተደሰትኩት ኢንስትራክተሮቹ ለመንግስቱ ወርቁ በሰጡት ክብር ነው” ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ

አጋራ
አጋራ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን በወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ለስልጠና መመደቡን አስታውቋል።

ከካፍ የደረሰውን መረጃ በፌስቡክ ገጹ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንደገለጸው ከ3 ሳምንት በፊት በላይቤሪያ ለኢንስትራክተሮች ኮርስ ሰጥተው የተመለሱት ኢንስትራክተር አብርሃም በቀጣዩ ሳምንት ወደ 20 ለሚጠጉ ለታንዛኒያ ኢንስትራክተሮች የሚሰጠውን ስልጠና እንዲሰጡ መመደባቸውን ካፍ አሳውቋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የተጠየቁት ኢንስትራክተር አብርሃም’ መብራቱ “በተጣለብኝ ሃላፊነት ተደስቻለሁ ለሀገሬ ባለሙያዎችም ትልቅ ሞራል ይሆናል በተገቢው መልኩ ስልጠናውን ሰጥቼ እንደምመለስም ርግጠኛ ነኝ”ሲሉ ተናግረዋል።

ኢንስትራክተር አብርሃም የተደሰቱበትን ገጠመኝንም እንዲህ ሲሉ ይናገራሉ.. “በላይቤሪያ ቆይታዬ የተደሰትኩት ኢንስትራክተሮቹ ለመንግስቱ ወርቁ በሰጡት ክብር ነው በላይቤሪያ ከአመታት በፊት የኤ ላይሰንስ የሰጣቸው ኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁ ነው ያኔ ኤ ላይሰንስ የወሰዱት አሁን ኢንስትራክተር ሆነዋል”ሲሉ የገጠማቸውን ገልጸዋል።

“የሀገር ባለውለታ የሆነውን የኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁን ህልፈት ብዙዎቹ አላወቁም ህልፈቱን ከሰሙ በኋላ በጣም አዝነዋል የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎትም አድርገናል”ሲሉ ተናግረዋል።

ኢንስትራክተር አብርሃም ከሰአታት በኋላ የሚገባውን አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ባስተላለፉት መልዕክት” አዲሱ አመት 2014 የሰላም የደስታ የጤናና ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ከፍ የምትልበት እንደ እግር ኳስ ደግሞ ክለቦቻችን የተሻለ ደረጃ የሚደርሱበት ብሄራዊ ቡድኑ የተሻለ ጉዞ የሚያደርግበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ ከአዲሱ ክለቤ ባህርዳር ከተማም ጥሩ ጊዜ እንደማሳልፍ ርግጠኛ ነኝ”ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...