ከሌሎቹ የሊጉ ክለቦች አንፃር ዘግየት ብለዉ ወደ ዝዉዉር ገበያው የገቡት ክትፎዎቹ በዛሬዉ ዕለት አይቮሪኮስታዊዉን ግብ ጠባቂ ሲላቫይን ጎቦሆ የግላቸው ማድረጋቸው ተሰምቷል።
በሀገሩ ለተለያዩ ክለቦች ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ ግብ ጠባቂዉ በአሁኑ ሰዓትም በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በይፋ ፊርማዉን እንደሚያኖር ታዉቋል።
በተያያዘም ወልቂጤ ከተማ በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ሀዋሳ በመጓዝ የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ተሰምቷል።
አስተያየት ይስጡ