መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ “በአዲሱ ዓመት ክለቤን ጠቅሜና ጥሩ ብቃቴን አሳይቼ ለብሔራዊ ቡድን መመረጥን አልማለው” ሱራፌል ጌታቸው /ድሬዳዋ ከተማ/
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችድሬዳዋ ከተማ

“በአዲሱ ዓመት ክለቤን ጠቅሜና ጥሩ ብቃቴን አሳይቼ ለብሔራዊ ቡድን መመረጥን አልማለው” ሱራፌል ጌታቸው /ድሬዳዋ ከተማ/

አጋራ
አጋራ

በድሬዳዋ ከተማ ክለብ ውስጥ በአማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተው ሱራፌል ጌታቸው በመጪው ዓመት በሚደረገው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ተሳትፎው ዘንድሮ ከነበረው ብቃቱ ይበልጥ በመሻሻል በጥሩ መልኩ እንደሚቀርብና ክለቡንም ለውጤታማነት ለማብቃት የሚቻለውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርግ ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፤ ሱራፌል ጌታቸው ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ያደረገው ቆይታም ይህንን ይመስላል፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ስለነበራቸው የዘንድሮ ተሳትፎ

“የውድድሩ አጀማመራችን ጥሩ ነበር፤ ባሳብነው መልኩ ደግሞ ፈፅሞ አልሄደልንም፤ ያም ሆኖ ግን ወደ መጨረሻ ጨዋታዎቹ አካባቢ ክለቡን ከመውረድ እንዲድን አትርፈነዋልና ያን በጥሩ መልኩ የማነሳው ነው”፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎአቸው ከውጤት ማጣት ጋር በተያያዘ ቡድናቸው ጋር ስለነበረው ችግር

“በጎል ማስቆጠሩ ላይ ጥቃቅን ችግሮች ነበሩብን፤ እነዚህ ችግሮች ደግሞ የብቃት ሳይሆኑ የአለመረጋጋትና የጉጉት ስለነበሩ ያ ብዙ ሊጎዳን ችሏል”፡፡

በድሬዳዋ ከተማ ክለብ ቆይታው መጪውን የውድድር ዘመን በምን መልኩ እንደሚያሳልፍ

“አሁን ላይ ክለባችንን በማጠናከሩ ረገድ አመራሮቻችን ጥሩ ነገር እየሰሩ ነው፤ ክፍተት ባሉብን ቦታዎች ላይ በአሰልጣኛችን ዘማሪያም አማካኝነት ተጨዋቾች የመጡልን ስለሆነ በውድድሩ ዘመኑ ጥሩ ቡድን ይዘን እንደምንቀርብ እምነቴ ነው፤ እኔም በዚህ ቡድን በሚኖረኝ ቆይታም እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ዘንድሮ ከነበረኝ አቋም በብዙ መልኩ በመሻሻል ጥሩ ሆኜ እንደምቀርብና ቡድኔንም ለውጤት እንደማበቃው እርግጠኛ ነኝ”፡፡

በቤትኪንጉ ዘንድሮ ፋሲል ከነማ ስለሳከው ሻምፒዮናነትና ስለ አቡበከር ኮከብነት ምን አልክ

“ፋሲል ከነማ በጣም ጥሩ ቡድን ነበር፤ ጎሎችን ያገባል፤ የሚያገኙትንም የግብ አጋጣሚዎችም ይጠቀሙ ነበርና ሻምፒዮናነታቸው የሚገባቸው ነው፤ የኢትዮጵያ ቡናውን አቡበከር ናስርን በተመለከተ በጣም ጎበዝ ተጨዋች ነው፤ እንቅስቃሴው ለአንድ ጥሩ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ደስ ይላል፤ ኳሶች እንደትሰጠው ያስገድድሃል፤ በተለይ እየሾለከ የሚሄድበት መንገድ የሚያስገርምም ነበርና በእሱ ኮከብነት በጣም ደስተኛ ነኝ፤ አድናቂውም ነኝ፤ በጣም የምወደውም ተጨዋች ነው”፡፡

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጋችን በዲ.ኤስ.ቲቪ መተላለፉ

“በዲ. ኤስ. ቲቪ ጨዋታዎቹ መተላለፋቸው በጣም ጥሩ ነገር ነው፤ በተለይ ለእኛ ሀገር ተጨዋቾች ችሎታቸውን ሊያሳድጉ የሚችሉበትን ብዙ ጥቅምን እየፈጠረላቸው ይገኛል፤ ከዛ ውጪም ሁሌም በኳሱ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ እንድትችልም በርትተህ እንድትሰራ ያደርግሃል፤ ከዛ ውጪም ለተመልካቹም ሜዳ ገብቶ ግጥሚያ ባይከታተል ራሱ ይህን ጨዋታ የሚመለከትበትና ጊዜውን የሚያሳልፍበትንም እድል አግኝቷልና ደስ ይላል፤ ይህ እንዲሳካ ያደረጉትም ሊመሰገኑም ይገባል”፡፡

ባሳለፋቸው የኳስ ህይወቱ ደስተኛ እንደሆነ

“ደስተኛ የሆንኩባቸው ጊዜያቶች እንዳሉ ሁሉ ሁሌም ደስተኛ አትሆንም፤ አንድ አንዴ ልትከፋ ትችላለህ፤ እኔ ለምሳሌ እንደ ደስታዬ ሁሉ የተከፋሁባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ ከእነዛ መካከልም አሳዳጊዬ ክለብ ሙገር ከሊጉ ሲወርድ በጣም አዝኛለው፤ ከዛ ውጪ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክለብ ውስጥ በነበርኩበት ሰዓት ጉዳት አጋጥሞኝ ሳለ ክለቡን እኔ በህግ እረታሁት እንጂ እኔን ችላ በማለት ያለምንም ነገር ሊያሰናብተኝ የፈለገበትን ነገር ሳስብ በጣም እከፋለውና እነዚህ ፈፅሞ የማይረሱኝ ናቸው”፡፡

ብዙዎች በእግር ኳሱ ላይ እንደነበረ ብቃት እስከ ብሔራዊ ቡድን ደረጃ መገኘት ነበረብህ ይሉሃል፤ ይሄ ያስቆጭሃል..

“በኳስ መቆጨትን አልፈልግም፤ ሁሉንም ነገር ፈጣሪ ሲለው ነው የሚሳካው፤ በኳሱ በአሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ ጊዜ ለታዳጊና ወጣት ብሔራዊ ቡድን ተመርጬ ለመጫወት ችያለው፤ በባሬቶም ጊዜ ከ23 ዓመት በታች ለሆናቸው ቡድን ተመርቼም የቡድኑ አባል ነበርኩ፤ እኔ ከዚህ በላይ ለመጓዝ ያልቻልኩት በምጫወትባቸው ክለቦች ውስጥ የውል ጊዜዎች ስለነበሩኝና ትላልቅ የሚባሉ ቡድኖችም ሊያስፈርሙኝ ያልቻሉበት ሁኔታ ስለነበር እድሉን ስላላገኘው ነው፤ አሁን ግን የሊግ ውድድሩ በዲ ኤስ ቲቪ እየታያ መሆኑ ለተጨዋቾች ብዙ ነገርን ስለሚፈጥር ጠንክሬ በመስራት ለብሔራዊ ቡድን ለመመረጥ ጥረትን አደርጋለው”፡፡

በመጨረሻ..

“ፈጣሪ ይመስገን፤ እዚህ ቦታ እንድደርስ ብዙ መሰናከሎችን አልፌያለው፤ ከእኔ ጎን ሆነው ድጋፍ ያደረጉልኝን አካላቶችና ቤተሰቦቼን አመሰግናለው”፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...